ኢዮብ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እርሱም ገና ይህን ሲናገር ሦስተኛው መልእክተኛ መጥቶ ለኢዮብ እንዲህ አለው፥ “ፈረሰኞች በሦስት ረድፍ ከብበው ግመሎችን ማርከው ወሰዱ፥ ብላቴኖችህንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “ከለዳውያን በሦስት ቡድን መጥተው ጥቃት አደረሱ፤ ግመሎችህንም ይዘው ሄዱ፤ አገልጋዮቹን በሰይፍ ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ይኸኛው መልእክተኛ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፥ “በሦስት ቡድን የተከፈሉ የከለዳውያን ዘራፊዎች በድንገት አደጋ ጣሉብን፤ ግመሎቹን በሙሉ ወሰዱአቸው፤ አገልጋዮችህንም በሙሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው። 参见章节 |