Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እና​ንተ ሴቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጆሮ​አ​ች​ሁም የአ​ፉን ቃል ትቀ​በል፤ ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ልቅ​ሶ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድ​ዋም ለባ​ል​ን​ጀ​ራዋ ዋይ​ታን ታስ​ተ​ምር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እናንተ ሴቶች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮቻችሁን ከአንደበቱ ለሚወጡት ቃላት ክፈቱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ዋይታ፣ አንዳችሁም ሌላውን ሙሾ አስተምሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እናንተ ሴቶች ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ ሴቶች፥ እግዚአብሔር የሚለውን አድምጡ፤ ቃሉንም ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ እንዴት ማልቀስ እንደሚገባቸው ሴቶች ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ ሙሾ የማውጣትንም ዘዴ ለወዳጆቻችሁ አስጠኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እናንተ ሴቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 9:20
15 交叉引用  

ከአ​ፉም ሕጉን ተቀ​በል፥ በል​ብ​ህም ቃሉን አኑር፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፥ “የጽ​ዮን ቆነ​ጃ​ጅት ኰር​ተ​ዋ​ልና፥ አን​ገ​ታ​ቸ​ውን እያ​ሰ​ገጉ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም እያ​ጣ​ቀሱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ረ​ገዱ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እየ​ጐ​ተቱ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም እያ​ማቱ ይሄ​ዳ​ሉና፤


በእ​ነ​ርሱ ላይ አለ​ቆ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ ጐል​ማ​ሶ​ችን እሾ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዘባ​ቾ​ችም ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል።


ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ከራ​ብና ከሰ​ይፍ የተ​ነሣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ይበ​ተ​ናሉ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እነ​ር​ሱ​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው አይ​ገ​ኝም።


ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ፤ ከን​ቱ​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ሳይ​ሆን ከገዛ ልባ​ቸው የወ​ጣ​ውን ራእይ ይና​ገ​ራሉ።


የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ ቍጣ​ዬን መላ​ሁ​ባ​ቸው፤ ታገ​ሥሁ፤ ፈጽ​ሜም አላ​ጠ​ፋ​ኋ​ቸ​ውም፤ በሜዳ በሕ​ፃ​ናት ላይ በጐ​ል​ማ​ሶ​ችም ጉባኤ ላይ መዓ​ቴን በአ​ን​ድ​ነት አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባል ከሚ​ስቱ ጋር ሽማ​ግ​ሌ​ውም ከጎ​በዙ ጋር ይያ​ያ​ዛ​ልና።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍ​ጣ​ውን ትው​ልድ ጥሎ​አ​ልና፥ ትቶ​ታ​ል​ምና ጠጕ​ር​ሽን ቈር​ጠሽ፥ ጣዪው፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ች​ሽም ሙሾ አው​ርጂ።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች?


ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ሣን። ብላ​ቴ​ና​ውና ሽማ​ግ​ሌው በመ​ን​ገ​ዶች ላይ ተጋ​ደሙ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ወድ​ቀ​ዋል፤ በረ​ኃብ ገደ​ል​ሃ​ቸው፤ በቍ​ጣ​ህም ቀን ሳት​ራራ አረ​ድ​ሃ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告