Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ምድ​ርን ትተ​ና​ልና፥ ቤቶ​ቻ​ች​ን​ንም ጥለን ሄደ​ና​ልና እን​ዴት ጐሰ​ቈ​ልን! እን​ዴት አፈ​ርን! የሚል የል​ቅሶ ድምፅ በጽ​ዮን ተሰ​ም​ቶ​አል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቷል፤ እንዲህም ይላል፤ ‘ምንኛ ወደቅን! ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው! ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤ አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በጽዮን፦ ‘እንዴት ተበዘበዝን! ምድሪቱንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አብዝተን አፈርን!’ የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በጽዮን “ወዮልን ልንጠፋ ነው! ፈጽሞም ተዋረድን! ቤቶቻችን ስለ ፈራረሱ አገራችንን ለቀን መሄዳችን ነው” እየተባለ የሚያስተጋባውን የለቅሶ ጩኸት አድምጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በጽዮን፦ እንዴት ተበዘበዝን! ምድርንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አፈርን! የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 9:19
20 交叉引用  

እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ፤ ድም​ፄ​ንም ስሙ፤ እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ምጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


“በውኑ እስ​ራ​ኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለ ምን ምርኮ ሆነ?


እነሆ! እንደ ደመና ይወ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረ​ሶ​ቹም ከን​ስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ናቸው። ተዋ​ር​ደ​ና​ልና ወዮ​ልን።


መከራ በመ​ከራ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አል፤ ምድር ሁሉ ተዋ​ር​ዳ​ለ​ችና፤ በድ​ን​ገ​ትም ድን​ኳኔ ጠፋ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም ተቀ​ዳ​ደዱ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን የኤ​ፍ​ሬ​ምን ዘር ሁሉ፥ እንደ ጣልሁ፥ እን​ዲሁ ከፊቴ እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


እኔን ያስ​ቈ​ጣ​ሉን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፊታ​ቸው ያፍር ዘንድ ለራ​ሳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍ​ጣ​ውን ትው​ልድ ጥሎ​አ​ልና፥ ትቶ​ታ​ል​ምና ጠጕ​ር​ሽን ቈር​ጠሽ፥ ጣዪው፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ች​ሽም ሙሾ አው​ርጂ።


ሳም​ኬት። እና​ንተ ከር​ኩ​ሳን ራቁ፥ አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉ​አ​ቸው፤ አት​ን​ኩ​አ​ቸ​ውም። ታው​ከ​ዋ​ልና ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ኖ​ሩ​ባት ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው።


ርስ​ታ​ችን ለሌላ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንም ለእ​ን​ግ​ዶች ሆኑ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አድ​ርግ።


ምድ​ሪ​ቱም ረከ​ሰች፤ ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ቷን በእ​ር​ስዋ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትተ​ፋ​ለች።


ምድ​ሪ​ቱም ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን ሕዝብ እንደ ተፋች ባረ​ከ​ሳ​ች​ኋት ጊዜ እና​ን​ተ​ንም እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


“እን​ግ​ዲህ ትቀ​መ​ጡ​ባት ዘንድ የማ​ገ​ባ​ችሁ ምድር እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም።


በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።


በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።


ዕውር በጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​ዳ​ብስ በቀ​ትር ጊዜ ትዳ​ብ​ሳ​ለህ፤ መን​ገ​ድ​ህም የቀና አይ​ሆ​ንም፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ የተ​ገ​ፋህ፥ የተ​ዘ​ረ​ፍ​ህም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም የለም።


跟着我们:

广告


广告