ኤርምያስ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የቀኑም ጥላ አልፎአልና ወዮልን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 “በርሷ ላይ ጦርነት ዐውጁ፤ ተነሡ በቀትር አደጋ እንጣልባት፤ ወዮ! ቀኑ እኮ መሸብን! ጥላው ረዘመ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 “በእርሷ ላይ ጦርነት አዘጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ።” “ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን!” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ጠላቶችዋም እንዲህ ይላሉ፦ “ኢየሩሳሌምን ለመውጋት እንዘጋጅ! ተነሡ! በእኩለ ቀን ላይ አደጋ እንጣልባት! እንዲያውም ዘግይተናል፤ ቀኑ ሊመሽ ተቃርቦአል፤ ፀሐይም ልትጠልቅ በመቃረብዋ ጥላው እየረዘመ ሄዶአል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን። 参见章节 |