Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ወና​ፉን የሚ​አ​ና​ፋው ደከመ፤ እር​ሳ​ሱም በእ​ሳት ቀለጠ፤ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውም መልሶ በከ​ንቱ ያቀ​ል​ጠ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ርሳሱን ለማቅለጥ፣ ወናፉ በብርቱ አናፋ፤ ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤ ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ወናፉ በኃይል አናፋ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፤ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል ነገረ ግን ኃጢአተኞች አልተወገዱም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እርሳሱን በእሳት ለማቅለጥ ወናፉ በኀይል ያናፋል፤ ክፉዎች ስላልተወገዱ ግን አንጥረኛው በከንቱ ይደክማል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ወናፉ አናፋ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፥ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል፥ ኃጢአተኞች አልተወገዱም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:29
12 交叉引用  

ብርና ወርቅ በከውር እንዲፈተን፥ የተመረጡ ሰዎች ልብም በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ ነው።


እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብት​መ​ለስ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ቴም ትቆ​ማ​ለህ፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም ከተ​ዋ​ረ​ደው ብት​ለይ እንደ አፌ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ርሱ ወደ አንተ ይመ​ለ​ሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነ​ርሱ አት​መ​ለ​ስም።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀ​ል​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እፈ​ት​ና​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እን​ደ​ዚሁ አደ​ር​ጋ​ለ​ሁና።


በከ​ንቱ ደከ​መች፤ ሆኖም ብዙ ዝገቷ ከእ​ር​ስዋ አል​ለ​ቀ​ቀም።


በር​ኵ​ሰ​ትሽ ሴሰ​ኝ​ነት አለ፤ አነ​ጻ​ሁሽ፤ አል​ነ​ጻ​ሽ​ምና መዓ​ቴን በላ​ይሽ እስ​ክ​ጨ​ርስ ድረስ እን​ግ​ዲህ ከር​ኵ​ሰ​ትሽ አት​ነ​ጺም።


ሕዝ​ቤም ከመ​ኖ​ሪ​ያው ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ብሩ ላይ ተቈጣ፤ ከፍ ከፍም አያ​ደ​ር​ገ​ውም።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


ወዳጆች ሆይ! በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤


ለእ​ና​ቱም ገን​ዘ​ቡን መለ​ሰ​ላት እና​ቱም ብሩን ወስዳ ከእ​ርሱ ሁለ​ቱን መቶ ብር ለአ​ን​ጥ​ረኛ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ረፀ ምስ​ልና ቀልጦ የተ​ሠራ ምስል አደ​ረ​ገው። በሚ​ካም ቤት አስ​ቀ​መ​ጡት።


跟着我们:

广告


广告