Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ሀገር ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰራዊት፣ ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤ ከምድር ዳርቻም፣ ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን አገር ይመጣል፥ ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻዎች ይነሣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሰሜን በኩል ከሚገኝ አገር ወራሪ ይመጣል፤ በሩቅ ያለ ታላቅ ሕዝብም ለጦርነት ተዘጋጅቶአል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን አገር ይመጣል፥ ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:22
18 交叉引用  

ወደ እኔ ብት​መ​ለሱ ግን፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም ምንም ከእ​ና​ንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበ​ተኑ፥ ከዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስሜም ይኖ​ር​በት ዘንድ ወደ መረ​ጥ​ሁት ስፍራ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነ​ሆም የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ባድ​ማና የሰ​ገኖ ማደ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ከሰ​ሜን ምድር ታላቅ መነ​ዋ​ወጥ መጥ​ቶ​አል።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ እነ​ዚ​ህን ከሰ​ሜን የሚ​መ​ጡ​ትን ተመ​ል​ከቺ፤ ለአ​ንቺ የሰ​ጠ​ሁሽ መንጋ፤ የክ​ብር በጎ​ችሽ ወዴት አሉ?


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕ​ዝብ ወደ ሕዝብ ይወ​ጣል፤ ጽኑም ዐውሎ ነፋስ ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የሚ​ያ​ስ​ፈራ ድምፅ ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ፍር​ሀት ነው እንጂ ሰላም አይ​ደ​ለም።


ለአ​ሕ​ዛብ አሳ​ስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላ​ቶች ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ላይ ይጮ​ኻሉ ብላ​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አውጁ።


ከሰ​ሜን ክፉ ነገ​ር​ንና ጽኑ ጥፋ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና ዓላ​ማ​ች​ሁን አንሡ፤ ወደ ጽዮ​ንም ሽሹ፥ ፍጠኑ፥ አት​ዘ​ግዩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰ​ሜን ይነ​ሣል፥ የሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም ፈሳሽ ይሆ​ናል፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱና በመ​ላዋ ሁሉ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱና በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ ይጐ​ር​ፋል፤ ሰዎ​ቹም ይጮ​ኻሉ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝ​ብን ከሩቅ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀያል ጥን​ታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋን​ቋ​ቸ​ው​ንም የማ​ታ​ው​ቀው፥ የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም የማ​ታ​ስ​ተ​ው​ለው ሕዝብ ነው።


ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ ሁሉም ኀያ​ላን ናቸው።


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


ቍጣ​ዬ​ንም አፈ​ስ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አና​ፋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ማጥ​ፋ​ት​ንም ለሚ​ያ​ውቁ ለጨ​ካ​ኞች ሰዎች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ነፍ​ስሽ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ለ​የች ወዳ​ጆ​ች​ሽን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥


跟着我们:

广告


广告