Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ባቢ​ሎን በድ​ን​ገት ወድቃ ተሰ​ባ​ብ​ራ​ለች፤ አል​ቅ​ሱ​ላት፤ ትፈ​ወ​ስም እንደ ሆነ ለቍ​ስ​ልዋ መድ​ኀ​ኒት ውሰ​ዱ​ላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ትሰበራለች፤ ዋይ በሉላት! ምናልባት ልትፈወስ ስለምትችል፣ ለቍስሏ የሚቀባ መድኀኒት ፈልጉላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ባቢሎን በድንገት ወደቀች ተሰበረችም፤ አልቅሱላት፥ ምናልባት ትፈወስ እንደሆነ ለቁስልዋ የሚቀባውን መድኃኒት ውሰዱላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ተሰብራለችና አልቅሱላት፤ ምናልባት ይፈወስ እንደ ሆነ ለቊስልዋ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ጠፍታለች፥ አልቅሱላት፥ ትፈወስም እንደ ሆነ ለቍስልዋ መድኃኒት ውሰዱላት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:8
20 交叉引用  

እነ​ሆም፥ በፈ​ረ​ሶች የሚ​ቀ​መጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚ​ሄዱ ፈረ​ሰ​ኞች ይመ​ጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ባቢ​ሎን ወደ​ቀች! ወደ​ቀች! ጣዖ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ፥ የእ​ጆ​ች​ዋም ሥራ​ዎች ሁሉ በም​ድር ላይ ተጥ​ለው ደቀቁ” አለ።


ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።


አሁን ግን በአ​ንድ ቀን እነ​ዚህ ሁለት ነገ​ሮች በድ​ን​ገት ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ትና መበ​ለ​ት​ነት ስለ መተ​ቶ​ችሽ ብዛ​ትና ስለ አስ​ማ​ቶ​ችሽ ጽናት ፈጽ​መው ይመ​ጡ​ብ​ሻል።


ድን​ግ​ሊቱ የግ​ብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለ​ዓድ ውጪ፤ የሚ​ቀባ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም ውሰጂ፤ ለም​ንም የማ​ይ​ጠ​ቅ​ም​ሽን መድ​ኀ​ኒት በከ​ንቱ አብ​ዝ​ተ​ሻል።


“ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ።


ሰለ​ዚህ ለሞ​አብ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ለሞ​አ​ብም ሁሉ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


“የም​ድ​ርም ሁሉ ክብር እን​ዴት ተያ​ዘች! እን​ዴ​ትስ ተወ​ሰ​ደች! ባቢ​ሎን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆነች!


በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?


“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥ ለቀኑ ወዮ!


ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?


ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤


跟着我们:

广告


广告