Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን የባ​ቢ​ሎ​ንን ምስ​ሎች የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ ምድ​ር​ዋም ሁሉ ትደ​ር​ቃ​ለች፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም የሞ​ቱት ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይወ​ድ​ቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 የባቢሎንን ጣዖታት የምቀጣበት ጊዜ፣ በርግጥ ይመጣልና። ምድሯ በሙሉ ትዋረዳለች፤ የታረዱትም በሙሉ በውስጧ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ያፈረች ትሆናለች ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ስለዚህም የባቢሎንን ጣዖቶች የማስወግድበት ጊዜ ይመጣል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ኀፍረት ይደርሳል፤ የተገደሉባት ልጆችዋ ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፥ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:47
13 交叉引用  

እነ​ሆም፥ በፈ​ረ​ሶች የሚ​ቀ​መጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚ​ሄዱ ፈረ​ሰ​ኞች ይመ​ጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ባቢ​ሎን ወደ​ቀች! ወደ​ቀች! ጣዖ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ፥ የእ​ጆ​ች​ዋም ሥራ​ዎች ሁሉ በም​ድር ላይ ተጥ​ለው ደቀቁ” አለ።


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ቸው በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በራብ ይሞ​ታሉ፤


አንቺ ትም​ህ​ርት ያስ​ተ​ማ​ር​ሻ​ቸው አለ​ቆ​ችሽ ሆነው በጐ​በ​ኙሽ ጊዜ ምን ትያ​ለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይ​ዝ​ሽ​ምን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም የሚ​ለ​ውን ነቢ​ይ​ንና ካህ​ንን፥ ሕዝ​ብ​ንም ያን ሰውና ቤቱን እቀ​ጣ​ለሁ።


“ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


ሥራ​ቸው ከንቱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጐ​በ​ኛ​ቸው ጊዜ ይጠ​ፋሉ።


በጽ​ዮን በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ በባ​ቢ​ሎ​ንና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከተ​ሞ​ችዋ ባድ​ማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት፥ የሰ​ውም ልጅ የማ​ያ​ል​ፍ​በት ምድር ሆኑ።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።


跟着我们:

广告


广告