Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረ​ገጠ አው​ድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመ​ከር ጊዜ ይደ​ር​ስ​ባ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ፣ የእህል መውቂያ ዐውድማ ናት፤ የመከር ወራቷም ፈጥኖ ይደርስባታል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አውድማ እንደ ተረገጠ ጊዜ፥ እንዲሁ የባቢሎን ልጅ ናት፥ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:33
15 交叉引用  

እርሱ ከመ​ከር በፊት አበባ በረ​ገፈ ጊዜ የወ​ይ​ንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወ​ይ​ኑን ቀጫ​ጭን ዘንግ በማ​ጭድ ይቈ​ር​ጣል፤ ጫፎ​ቹ​ንም ይመ​ለ​ም​ላል፤ ያስ​ወ​ግ​ድ​ማል።


እና​ንተ የተ​ረ​ፋ​ች​ሁና መከራ የም​ት​ቀ​በሉ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረ​ኝ​ንና የሰ​ማ​ሁ​ትን ስሙ።


አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።


መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”


ይሁዳ ሆይ! የሕ​ዝ​ቤን ምርኮ በም​መ​ል​ስ​በት ጊዜ ለአ​ንተ ደግሞ መከር ተወ​ስ​ኖ​ል​ሃል።”


መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች በብ​ረት መጋዝ ሰን​ጥ​ቀ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደ​ማ​ስቆ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን አሳብ አያውቁም፥ ምክሩንም አያስተውሉም፥ እንደ ነዶ ወደ አውድማ አከማችቶአቸዋልና።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።


በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፣ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው።


ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን “እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ፤” እላለሁ’ አለ።”


እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፤ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፤ አጫጆችም መላእክት ናቸው።


跟着我们:

广告


广告