Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የባ​ቢ​ሎን ተዋ​ጊ​ዎች መዋ​ጋ​ትን ትተ​ዋል፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ጠፍ​ቶ​አል፤ እንደ ሴቶ​ችም ሆነ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ነድ​ደ​ዋል፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የባቢሎን ጦረኞች መዋጋት ትተዋል፤ በምሽጎቻቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸው ተሟጥጧል፤ እንደ ሴት ሆነዋል፤ በማደሪያዎቿም እሳት ተለኵሷል፤ የደጇም መወርወሪያ ተሰብሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፥ ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፥ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:30
16 交叉引用  

የድ​ሮ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ዓመ​ታት ዐሰ​ብሁ፤ አነ​በ​ብ​ኹም፤


በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ወ​ር​ድ​ባ​ቸው ፍር​ሀ​ትና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ የተ​ነሣ ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ።


እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ከነ​በ​ል​ባል ኀይል አያ​ድ​ኑም፤ እንደ እሳ​ትም ፍም ይሆ​ኑ​ብ​ሻል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።


ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


እጆ​ችዋ ደክ​መ​ዋ​ልና ክበ​ቡ​አት፤ ግንቧ ወድ​ቋል፤ ቅጥ​ር​ዋም ፈር​ሶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀል ነውና ተበ​ቀ​ሏት፤ እንደ ሠራ​ች​ውም ሥሩ​ባት።


መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”


መሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋ​ንና ጥበ​በ​ኞ​ች​ዋ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንና ሹሞ​ች​ዋን፥ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ዋ​ንም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ለው ንጉሥ።


ጤት። በሮ​ችዋ በመ​ሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​በሩ፤ ንጉ​ሥ​ዋና አለ​ቃዋ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አሉ፤ ሕግም የለም። ነቢ​ያ​ቷም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራእይ አላ​ዩም።


የደ​ማ​ስ​ቆ​ንም ቍል​ፎች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በአ​ዎን ሸለቆ የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች አጠ​ፋ​ለሁ፤ የካ​ራን ሰዎች ወገ​ኖ​ች​ንም እቈ​ራ​ር​ጣ​ለሁ፤ የሶ​ርያ ሕዝ​ብም ወደ ቂር ይማ​ረ​ካሉ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል።


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


跟着我们:

广告


广告