ኤርምያስ 50:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ወደ ጽዮን የሚሄዱበትን ጎዳና ይመረምራሉ፤ ፊታቸውንም ወደ ሀገራቸው ይመልሳሉ፤ የዘለዓለም ቃልኪዳን አይረሳምና መጥተው ወደ ፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ይማጠናሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ ፊታቸውንም ወደዚያ ያቀናሉ። መጥተውም ከቶ በማይረሳ፣ በዘላለም ቃል ኪዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋራ ይጣበቃሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ወደ ጽዮን የሚያደርሰውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ አቅጣጫውንም ተከትለው ይጓዛሉ፤ ከእኔም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ከቶም አያፈርሱትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘላለም ቃል ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ተጠጉ ብለው ስለ ጽዮን መንገድ ይጠይቃሉ። 参见章节 |