Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 50:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ከተ​ሞች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ ሰው በዚያ አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰ​ውም ልጅ አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፣ በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀረኋቸው” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ጎረቤቶቻቸውን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ሰዶምንና ገሞራን በአካባቢያቸው ካሉ ከተሞች ጋር በደመሰስኩ ጊዜ እንደሆነው እንዲሁም በባቢሎን ማንም እንደገና ሰፍሮ መኖር አይችልም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 50:40
15 交叉引用  

የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


ሰዶ​ምና ገሞራ፥ በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የነ​በ​ሩት ከተ​ሞች እንደ ተገ​ለ​በጡ፥ ይላል ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ በዚያ ሰው አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰው ልጅም አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።


ከአ​ን​ተም ለማ​ዕ​ዘን የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይ​ንና ለመ​ሠ​ረት የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይን አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አጠ​ፋ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን አስ​ቀ​ድሜ እንደ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ቸው፥ እን​ዲሁ ገለ​በ​ጥ​ኋ​ችሁ፤ እና​ን​ተም ከእ​ሳት ውስጥ እንደ ተነ​ጠቀ ትን​ታግ ሆና​ችሁ፤ በዚ​ህም ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም አስ​ቀ​ድሞ እንደ ተና​ገረ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸባ​ኦት ዘር ያስ​ቀ​ረ​ልን ባይ​ሆን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፥ ገሞ​ራ​ንም በመ​ሰ​ልን ነበር።”


ምድ​ርም በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ ዲንና ጨው፥ መቃ​ጠ​ልም እንደ ሆነ​ባት፥ እን​ዳ​ይ​ዘ​ራ​ባ​ትም፥ እን​ዳ​ታ​በ​ቅ​ልም፥ ማና​ቸ​ውም ሣርና ልም​ላ​ሜም እን​ዳ​ይ​ወ​ጣ​ባት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣ​ውና በመ​ዓቱ እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ እንደ አዳ​ማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥


እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፤ እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።


跟着我们:

广告


广告