Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 50:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ! አን​ቺን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ፥ ቀንሽ ደር​ሶ​አ​ልና እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “አንተ ትዕቢተኛ፤ እነሆ፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “የምትቀጣበት ጊዜ፣ ቀንህ ደርሷልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ትዕቢተኛው ሆይ! የመጐብኘትህ ጊዜ፥ ቀንህ ደርሶአልና እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “ትዕቢተኛይቱ ባቢሎን ሆይ! እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በአንቺ ላይ እነሣለሁ፤ አንቺንም የምቀጣበት ጊዜ ደርሶአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ትዕቢተኛው ሆይ፥ የመጐብኘትህ ጊዜ፥ ቀንህ ደርሶአልና እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 50:31
20 交叉引用  

የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤


እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድን​ጋ​ያማ ሸለቆ የም​ት​ቀ​መጥ ሆይ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እና​ን​ተም፦ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠን ወይም ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችን የሚ​ገባ ማን ነው? የም​ትሉ ሆይ! እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፤


የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።


በዓ​ለት ንቃ​ቃት ውስጥ የም​ት​ቀ​መጥ፥ የተ​ራ​ራ​ውን ከፍታ የም​ት​ይዝ ሆይ! ድፍ​ረ​ት​ህና የል​ብህ ኵራት አነ​ሣ​ሥ​ተ​ው​ሃል። ቤት​ህ​ንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታ​ደ​ርግ፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።


አንቺ ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ!፥ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለ​ሽም፤ የሚ​ያ​ነ​ሳ​ሽም የለም፤ በዛ​ፎ​ችሽ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያሽ ያለ​ው​ንም ሁሉ ትበ​ላ​ለች።”


“አንተ ምድ​ርን ሁሉ የም​ታ​ጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ከድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ላይ አን​ከ​ባ​ል​ል​ሃ​ለሁ፤ የተ​ቃ​ጠ​ለም ተራራ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ።


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ፥ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ ትን​ቢ​ትን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ፍር​ድን በመ​ካ​ከ​ልሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፣ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።


እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።


ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


跟着我们:

广告


广告