Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 50:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣ ተገኘሽ፤ ተያዝሽም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ባቢሎን ሆይ! አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከጌታ ጋር ስለ ታገልሽ ተገኝተሻል ተይዘሻልም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ባቢሎን ሆይ! በራስሽ ላይ ባጠመድሽው ወጥመድ ሳታውቂው ተያዝሽበት፤ ተይዘሽ የተጋለጥሽውም እግዚአብሔርን ስለ ተዳፈርሽ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ባቢሎን ሆይ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 50:24
17 交叉引用  

እጁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዘር​ግ​ቶ​አ​ልና፥ ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም አን​ገ​ቱን አደ​ን​ድ​ኖ​አ​ልና።


“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክንድ ያለ ክንድ አለ​ህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታን​ጐ​ደ​ጕ​ዳ​ለ​ህን?


በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።


በዓ​ለም ሁሉ ላይ ክፋ​ትን አዝ​ዛ​ለሁ፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ኀጢ​አት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም ኵራት እሽ​ራ​ለሁ፤ የጨ​ካ​ኞ​ቹ​ንም ኵራት አዋ​ር​ዳ​ለሁ።


“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን?


በሞ​አብ የም​ት​ኖር ሆይ! ፍር​ሀ​ትና ጕድ​ጓድ፥ ወጥ​መ​ድም በአ​ንተ ላይ አሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


እር​ስ​ዋን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ዓመት በሞ​አብ ላይ ይህን አመ​ጣ​ለሁ፤ በፍ​ር​ሀት የሸሸ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድ​ቃል፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


መሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋ​ንና ጥበ​በ​ኞ​ች​ዋ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንና ሹሞ​ች​ዋን፥ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ዋ​ንም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ለው ንጉሥ።


ባቢ​ሎን በድ​ን​ገት ወድቃ ተሰ​ባ​ብ​ራ​ለች፤ አል​ቅ​ሱ​ላት፤ ትፈ​ወ​ስም እንደ ሆነ ለቍ​ስ​ልዋ መድ​ኀ​ኒት ውሰ​ዱ​ላት።


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


跟着我们:

广告


广告