Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሞአ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰር​ታ​ለ​ችና ሕዝብ ከመ​ሆን ትጠ​ፋ​ለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሏልና ይጠፋል፤ መንግሥትነቱም ይቀራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ሞዓብም በጌታ ላይ ኰርቶአልና ከእንግዲህ ወድያ ሕዝብ አይሆንም፥ እርሱም ይጠፋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ሞአብ በእኔ ላይ ስለ ታበየች ትደመሰሳለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ በመንግሥትነት አትታወቅም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሞዓብም በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና ሕዝብ ከመሆን ይጠፋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:42
14 交叉引用  

ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።


የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማንን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ህ​በት፥ ዐይ​ን​ህ​ንስ ወደ ላይ ያነ​ሣ​ህ​በት ማን ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ አይ​ደ​ለ​ምን?


የአ​ራም ራስ ደማ​ስቆ ነው፤ የደ​ማ​ስ​ቆም ራስ ረአ​ሶን ነው፤ በስ​ድሳ አም​ስት ዓመት ውስጥ የኤ​ፍ​ሬም መን​ግ​ሥት ከሕ​ዝብ ይጠ​ፋል፤


አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሞ​አብ ፈውስ የለም፤ በሐ​ሴ​ቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እን​ዳ​ት​ሆን እና​ጥ​ፋት” ብለው ክፉ ነገ​ርን አስ​በ​ው​ባ​ታል። ፈጽሞ ትተ​ዋ​ለች፤ ከኋ​ላዋ ሰይፍ ይመ​ጣ​ልና።


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።


跟着我们:

广告


广告