Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ስለ ሞአብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍ​ታ​ለ​ችና ወዮ​ላት! ቂር​ያ​ታ​ይም አፍ​ራ​ለች፤ ተይ​ዛ​ማ​ለች፤ መጠ​ጊ​ያ​ዋም አፍ​ራ​ለች፤ ደን​ግ​ጣ​ማ​ለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛለችም፤ አምባይቱም አፍራለች ፈርሳለችም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ሞአብ የሚለው ይህ ነው፦ “ነቦ ስለምትደመሰስ፥ ለነቦ ሕዝብ ወዮላቸው! ቂርያታይም በጠላት እጅ ትወድቃለች፤ ብርቱ የሆኑ ምሽጎችዋም ይደመሰሳሉ፤ ሕዝብዋም በዕፍረት ላይ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ስለ ሞዓብ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛማለች፥ ሚሥጋብ አፍራለች ደንግጣማለች።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:1
19 交叉引用  

በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ርና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ረዐ​ይ​ትን በአ​ስ​ጣ​ሮት ቃር​ና​ይም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን ሰዎ​ች​ንና ኦሚ​ዎ​ስን በሴዊ ከተማ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤


ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው።


አሁ​ንም እነሆ፥ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያል​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ ያል​ፈ​ቀ​ድ​ህ​ላ​ቸው የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆች፥ የሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጠ​ናል፤ እህ​ልም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ጭድም በጭቃ እን​ደ​ሚ​በ​ራይ እን​ዲሁ ሞዓብ ይረ​ገ​ጣል።


የተ​መ​ሸ​ገ​ው​ንና ከፍ ከፍ ያለ​ው​ንም ቅጥ​ር​ህን ዝቅ ያደ​ር​ገ​ዋል። ያዋ​ር​ደ​ው​ማል፤ ወደ መሬ​ትም እስከ አፈር ድረስ ይጥ​ለ​ዋል።


እኔ የጸ​ናች ከተማ ነኝ፤ አን​ድ​ዋን ከተማ ይወ​ጋሉ። በከ​ንቱ አጠ​ጣ​ኋት፤ በሌ​ሊት ትጠ​መ​ዳ​ለች፤ በቀ​ንም ግድ​ግ​ዳዋ ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ያ​ነ​ሣ​ትም የለም።


ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፤


ወደ ይሁዳ ንጉ​ሥም ወደ ሴዴ​ቅ​ያስ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓ​ብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮ​ስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶ​ናም ንጉሥ ላክ።”


አሕ​ዛብ ሁሉ ያል​ተ​ገ​ረዙ ናቸ​ውና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ልባ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረዘ ነውና የተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሁሉ፥ ግብ​ጽ​ንና ይሁ​ዳን፥ ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ በም​ድረ በዳም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ጠጕ​ራ​ቸ​ውን በዙ​ሪያ የተ​ላ​ጩ​ት​ንም ሁሉ የም​ጐ​በ​ኝ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል።”


አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤


ከጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይ​ምም ተጕ​ዘው በና​ባው ፊት ባሉት በአ​ባ​ሪም ተራ​ሮች ላይ ሰፈሩ።


ቂር​ያ​ታ​ይም፥ ሴባማ፥ ሲራ​ዳት፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም ተራራ ያለ​ችው ሲዮን፥


跟着我们:

广告


广告