ኤርምያስ 46:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በፈረሶች ተቀመጡ፤ ሰረገሎችንም አዘጋጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የሊብያ ኀያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኀያላን ይውጡ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ፈረሶች ሆይ ዘልላችሁ ውጡ፤ ሠረገሎችም ሸምጥጡ፤ ጋሻ ያነገባችሁ የኢትዮጵያና የፉጥ ሰዎች፣ ቀስት የገተራችሁ የሉድ ጀግኖች፣ እናንተ ብርቱ ጦረኞች ተነሥታችሁ ዝመቱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ፈረሶች ሆይ! ውጡ፤ ሰረገሎችም ሆይ! ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ፈረሶች ወደ ፊት እንዲሄዱ፥ ሠረገሎችም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ እዘዙ፤ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ ጋሻቸውን አንግበው በመጡ ሰዎችና፥ ከልድያ በመጡ ቀስት በሚወረውሩ ኀያላን ሰዎች ጭምር የተጠናከሩ ወታደሮችን ላኩ” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ፈረሶች ሆይ፥ ውጡ፥ ሰረገሎችም ሆይ፥ ንጐዱ፥ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ። 参见章节 |