Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 46:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ድን​ግ​ሊቱ የግ​ብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለ​ዓድ ውጪ፤ የሚ​ቀባ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም ውሰጂ፤ ለም​ንም የማ​ይ​ጠ​ቅ​ም​ሽን መድ​ኀ​ኒት በከ​ንቱ አብ​ዝ​ተ​ሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ድንግሊቱ የግብጽ ሴት ልጅ ሆይ፤ ወደ ገለዓድ ውጪ፤ የሚቀባ መድኀኒትም አምጪ፤ ነገር ግን መድኀኒት የምታበዢው በከንቱ ነው፤ ፈውስ አታገኚም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፤ ብዙ መድኃኒቶችን የተጠቀምሺው በከንቱ ነው፤ ለአንቺ መዳኛ የለሽም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንደ ድንግል የምትታዪ ግብጽ ሆይ! ወደ ገለዓድ ሄደሽ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጊ፤ የአንቺ መድኃኒት ሁሉ ከንቱ ነው፤ ሊፈውስሽ የሚችል ነገር ከቶ የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ፥ ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፥ መድኃኒትን ያበዛሽው በከንቱ ነው፥ መዳን የለሽም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 46:11
15 交叉引用  

እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።


አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።


አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


“ለራ​ስሽ የመ​ን​ገድ ምል​ክት አድ​ርጊ፥ መን​ገ​ድ​ንም የሚ​መሩ ዐም​ዶ​ችን ትከዪ፤ ልብ​ሽ​ንም ወደ ሄድ​ሽ​በት መን​ገድ ወደ ጥር​ጊ​ያው አቅኚ፤ አንቺ የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ! ተመ​ለሺ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ወደ ከተ​ሞ​ችሽ እያ​ለ​ቀ​ስሽ ተመ​ለሺ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ እንደ ገና እሠ​ራ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም ትሠ​ሪ​ያ​ለሽ፤ እንደ ገናም ከበ​ሮ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ከዘ​ፋ​ኞች ጋር ትወ​ጫ​ለሽ።


ባቢ​ሎን በድ​ን​ገት ወድቃ ተሰ​ባ​ብ​ራ​ለች፤ አል​ቅ​ሱ​ላት፤ ትፈ​ወ​ስም እንደ ሆነ ለቍ​ስ​ልዋ መድ​ኀ​ኒት ውሰ​ዱ​ላት።


በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ስን​ዴ​ንም ይሸ​ም​ቱ​ልሽ ነበር፤ ሰሊ​ሆ​ት​ንና በለ​ሶ​ንን፥ ዘይ​ት​ንና የተ​ወ​ደደ ማርን፥ ርጢ​ን​ንም ከአ​ንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?


እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።


跟着我们:

广告


广告