Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 44:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ​ዚህ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ በሚ​ኖር በይ​ሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ተብሎ እን​ዳ​ይ​ጠራ፥ እነሆ በታ​ላቁ ስሜ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በግብጽ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብጽ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ‘ሕያው በሆነ ጌታ እግዚአብሔር እምላለሁ!’ ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ነገር ግን በግብጽ ስለምትኖሩ እስራኤላውያን ሁሉ እኔ እግዚአብሔር በኀያሉ ስሜ በመማል የወሰንኩትን ስሙ፤ ከእናንተ ማንም ሰው ‘ሕያው ልዑል እግዚአብሔርን’ ብሎ በስሜ እንዲምል አልፈቅድም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 44:26
28 交叉引用  

“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ለም​ት​ወ​ድ​ደው ልጅ​ህም ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ምና መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤


መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብት​ወ​ድ​ድስ በሰ​ጠ​ሁህ ነበር፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አት​ወ​ድ​ድም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በእ​ር​ግጥ ለጠ​ላ​ቶ​ችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህ​ል​ሽን አል​ሰ​ጥም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ትን ወይ​ን​ሽን አይ​ጠ​ጡም፤” ብሎ በጌ​ት​ነ​ቱና በክ​ንዱ ኀይል ምሎ​አል።


ነገር ግን ይህን ቃል ባት​ሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እን​ዲ​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፤ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በዚች ሀገር የሚ​ቀ​ሩ​ት​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅሬታ፥ በግ​ብ​ጽም ሀገር የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


“ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁ​ዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክ​ፋት በላ​ያ​ችሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”


ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ ለሴ​ቶ​ቹም ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እኔ ሕያው ነኝና በተ​ራ​ሮች መካ​ከል እን​ዳለ እንደ አጤ​ቤ​ር​ዮን፥ በባ​ሕ​ርም አጠ​ገብ እን​ዳለ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ እን​ዲሁ በእ​ው​ነት ይመ​ጣል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰ​ደ​ቢ​ያና መረ​ገ​ሚ​ያም እን​ድ​ት​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ይሆ​ናሉ።


እነ​ር​ሱም፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ቢሉ የሚ​ም​ሉት በሐ​ሰት ነው።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በራሱ ምሎ​አል፦ በእ​ው​ነት ሰዎ​ችን እንደ አን​በጣ እሞ​ላ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም እየ​ሮጡ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሻል።”


ብት​ገ​ድ​ሉም፥ ብታ​መ​ነ​ዝ​ሩም፥ ብት​ሰ​ር​ቁም፥ በሐ​ሰ​ትም ብት​ምሉ፥ ለበ​አ​ልም ብታ​ጥኑ፥ የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ው​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ ክፉ ያገ​ኛ​ች​ኋል።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱ​ሱን ስሜ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና በመ​ባ​ችሁ አታ​ር​ክሱ።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! አንተ አላ​ዋቂ አት​ሁን፤ አን​ተም ይሁዳ! ወደ ጌል​ጌላ አት​ሂድ፤ ወደ ቤት​አ​ዊ​ንም አት​ውጡ፤ በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ማሉ።


አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተ​ሰ​ቦ​ቻ​ቸው በወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባ​ቂ​ውን በአ​ንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአ​ለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እን​ዳ​ት​ጠራ ዝም በል ይለ​ዋል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ትዕ​ቢት አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ሀገ​ሮ​ቹ​ንም ጠላሁ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ከሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ሰዎች ጋር አጠ​ፋ​ለሁ” ብሎ በራሱ ምሎ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በያ​ዕ​ቆብ ትዕ​ቢት እን​ዲህ ብሎ ምሎ​አል፥ “ሥራ​ች​ሁን ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምንም አል​ረ​ሳም።


እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆ​ሮዬ እንደ ተና​ገ​ራ​ች​ሁት እን​ዲሁ በእ​ው​ነት አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከካ​ዱት በቀር ወደ ዕረ​ፍቱ እን​ዳ​ይ​ገቡ በማን ላይ ማለ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ዉን በሰ​ጠው ጊዜ ይም​ል​በት ዘንድ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ባይ​ኖር፥ በራሱ ማለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


跟着我们:

广告


广告