Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 44:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በመ​ዐት እንደ ጐበ​ኘሁ፥ እን​ዲሁ በግ​ብፅ ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም እጐ​በ​ኛ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኢየሩሳሌምን እንደ ቀጣሁ፣ በግብጽ የሚኖሩትን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እቀጣለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኢየሩሳሌምን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንደ ቀጣሁ፥ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን እቀጣለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ኢየሩሳሌምን በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር እንደቀጣሁ፥ በግብጽ የሚኖሩትንም እቀጣለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኢየሩሳሌምንም እንደ ቀጣሁ፥ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 44:13
11 交叉引用  

ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ቸው በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በራብ ይሞ​ታሉ፤


በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”


በማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም ስፍራ ሁሉ ለስ​ድ​ብና ለም​ሳሌ፥ ለጥ​ላ​ቻና ለር​ግ​ማን ይሆኑ ዘንድ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤


እና​ንተ የም​ት​ፈ​ሩት ሰይፍ በዚያ በግ​ብፅ ምድር ያገ​ኛ​ች​ኋል፤ ስለ እር​ሱም የም​ት​ደ​ነ​ግ​ጡ​በት ራብ በዚያ በግ​ብፅ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።


ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን በሚ​ያ​ቀኑ ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ያል​ቃሉ፤ እኔም ከማ​መ​ጣ​ባ​ቸው ክፉ ነገር ማንም አይ​ቀ​ርም፤ ማንም አያ​መ​ል​ጥም።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ቍጣ​ዬና መቅ​ሠ​ፍቴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እን​ዲሁ ወደ ግብፅ በገ​ባ​ችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈ​ስ​ስ​ባ​ች​ኋል፤ እና​ን​ተም ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት ለስ​ድ​ብና ለር​ግ​ማን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይች​ንም ስፍራ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ዩ​አ​ትም።


መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።


跟着我们:

广告


广告