Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 43:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪ​ያ​ዬን የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ ዙፋ​ኑ​ንም እኔ በሸ​ሸ​ግ​ኋ​ቸው በእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ ጋሻ​ዎ​ቹ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ ያነ​ሣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲህም በላቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ ዙፋኑንም እዚህ በቀበርኋቸው ድንጋዮች ላይ እዘረጋለሁ፤ የንጉሥ ድንኳኑንም በላያቸው ይተክላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲህም በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባርያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፥ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም የዙፋኑን ድንኳን በላያቸው ይዘረጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚያም የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አገልጋዬ የሆነውን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ወደዚህ ስፍራ አምጥቼ አንተ በቀበርካቸው በእነዚያ ድንጋዮች ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ የቤተ መንግሥት ድንኳኖቹን የሚተክልባቸው መሆኑን ንገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፥ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፥ እርሱም ማለፊያውን ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 43:10
19 交叉引用  

የጾም አዋ​ጅም ነገሩ፤ ናቡ​ቴ​ንም በሕ​ዝቡ ፊት በከ​ፍ​ተኛ ቦታ አስ​ቀ​መ​ጡት።


አክ​ዓ​ብም ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወ​ር​ሰው ተነ​ሥቶ ወረደ።


ባሪ​ያህ ደግሞ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ በመ​ጠ​በ​ቁም ብዙ ዋጋ ይቀ​በ​ላል።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ወደ እጆ​ቹም ተግ​ባር አላ​ሰ​ቡ​ምና አፍ​ር​ሳ​ቸው፥ አት​ሥ​ራ​ቸ​ውም።


ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦


እነሆ እኔ በሰ​ሜን ያሉ​ትን የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቱን ወገ​ኖች ሁሉ እጠ​ራ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር መግ​ቢያ በዙ​ሪ​ያ​ዋና በቅ​ጥ​ርዋ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ላይ ዙፋ​ና​ቸ​ውን ያስ​ቀ​ም​ጣሉ።


“ታላ​ላ​ቆ​ችን ድን​ጋ​ዮች በእ​ጅህ ውሰድ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች እያዩ በጣ​ፍ​ናስ ባለው በፈ​ር​ዖን ቤት ደጅ መግ​ቢያ ሸሽ​ጋ​ቸው።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እን​ደ​ሚ​መ​ጣና የግ​ብ​ፅን ምድር እን​ደ​ሚ​መታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለነ​ቢዩ ለኤ​ር​ም​ያስ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።


ዙፋ​ኔ​ንም በኤ​ላም አኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ንጉ​ሡ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አጠ​ፋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


跟着我们:

广告


广告