Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 42:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አሁ​ንም ሄዳ​ችሁ እን​ድ​ት​ቀ​መጡ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​በት ስፍራ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እን​ድ​ት​ሞቱ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እንግዲህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በርግጥ ዕወቁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህም አሁን ሄዳችሁ ለመቀመጥ በወደዳችሁበት በዚያ ስፍራ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንደምትሞቱ በእርግጥ እወቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለዚህ አሁን ሄዳችሁ ልትኖሩ በምትፈልጉበት ቦታ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንደምትሞቱ እርግጠኞች ሁኑ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 42:22
10 交叉引用  

ስለ​ዚህ የፈ​ር​ዖን ኀይል እፍ​ረት፥ በግ​ብፅ መታ​መ​ንም ስድብ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”


ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን በሚ​ያ​ቀኑ ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ያል​ቃሉ፤ እኔም ከማ​መ​ጣ​ባ​ቸው ክፉ ነገር ማንም አይ​ቀ​ርም፤ ማንም አያ​መ​ል​ጥም።


መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን ያቀ​ኑ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ሁሉም ይጠ​ፋሉ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ፤ ከታ​ና​ሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ይሞ​ታሉ፤ ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት፥ ለመ​ረ​ገ​ሚ​ያና ለመ​ሰ​ደ​ቢያ ይሆ​ናሉ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች ያሉ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በም​ድረ በዳ ያለ​ውን ለአ​ራ​ዊት መብል አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ችና በዋ​ሻ​ዎች ያሉ በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ጅህ አጨ​ብ​ጭብ፤ በእ​ግ​ር​ህም አሸ​ብ​ሽብ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤት ርኵ​ሰት ሁሉ ወዮ ወዮ በል፤ በረ​ኀ​ብና በጦር፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይጠ​ፋሉ።


በሩቅ ያለው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በቅ​ር​ብም ያለው በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ በሀ​ገር የቀ​ረ​ውና የተ​ከ​በ​በ​ውም በራብ ይሞ​ታል፤ እን​ዲሁ መዓ​ቴን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።


跟着我们:

广告


广告