Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 42:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን በሚ​ያ​ቀኑ ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ያል​ቃሉ፤ እኔም ከማ​መ​ጣ​ባ​ቸው ክፉ ነገር ማንም አይ​ቀ​ርም፤ ማንም አያ​መ​ል​ጥም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በዚያም ለመኖር ወደ ግብጽ ለመሄድ የወሰኑ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር በርግጥ ይሞታሉ፤ ከማመጣባቸውም ጥፋት አንድ እንኳ የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይገኝም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታሉ፤ እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ከእነርሱ አንድም ሰው በሕይወት አይተርፍም፥ አንድም ሰው አያመልጥም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ወደ ግብጽ ሄደው ለመኖር የወሰኑ ሁሉ፥ በጦርነት ወይም በራብ ወይም በወረርሽኝ ያልቃሉ፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ አይተርፍም፤ በእነርሱ ላይ ላመጣው ካቀድኩት መቅሠፍትም የሚያመልጥ አይኖርም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ ግብጽም ይገቡ ዘንድ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን በሚያቀኑ ሰዎች ሁሉ እንዲህ ይሆንባቸዋል፥ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታሉ፥ እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ማንም አይቀርም፥ ማንም አያመልጥም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 42:17
7 交叉引用  

ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ወጣ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ነፍ​ሱም እንደ ምርኮ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለች፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራል።


ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤


አሁ​ንም ሄዳ​ችሁ እን​ድ​ት​ቀ​መጡ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​በት ስፍራ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እን​ድ​ት​ሞቱ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።”


ከሰ​ይ​ፍም የሚ​ያ​መ​ልጡ በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሰዎች ከግ​ብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለ​ሳሉ፤ ሊቀ​መ​ጡም ወደ ግብፅ ምድር የገ​ቡት የይ​ሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእ​ነ​ርሱ የማ​ና​ችን ቃል እን​ዲ​ጸና ያው​ቃሉ።


ሰይ​ፍን ትፈ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


跟着我们:

广告


广告