Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 41:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እስ​ማ​ኤ​ልም ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣ​ለ​በት ጕድ​ጓድ ንጉሡ አሳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ባኦ​ስን ስለ ፈራ የሠ​ራው ጕድ​ጓድ ነበረ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሞላ​በት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እስማኤል ከጎዶልያስ በተጨማሪ የገደላቸው ሰዎች ሁሉ ሬሳ የተጣለበት የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ፣ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ ለመከላከል ያሠራው ነበር፤ ይህን ጕድጓድ የናታንያ ልጅ እስማኤል በሬሳ ሞላው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ለመመከት የሠራው ምሽግ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነዚያን ሰዎች ገድሎ የጣለበትም ያ ጒድጓድ የእስራኤል ንጉሥ ባዕሻ አደጋ በጣለበት ጊዜ ንጉሥ አሳ ለመጠባበቂያ አስቈፍሮት የነበረ ትልቅ ጒድጓድ ነበር፤ እስማኤል ያን ጒድጓድ በሬሳ ሞላው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፥ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 41:9
11 交叉引用  

በተ​ራ​ራው ላይ፥ ያም ባይ​ሆን በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ው​ሮ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ ፊተ​ኞቹ ቢወ​ድቁ የሚ​ሰ​ማው ሁሉ አቤ​ሴ​ሎ​ምን የተ​ከ​ተለ ሕዝብ ተመታ ይላል።


አንተ ግን በጦር ተወ​ግ​ተው ወደ መቃ​ብር ከሚ​ወ​ርዱ ብዙ ሙታን ጋር እንደ ረከሰ ሬሳ በተ​ራ​ሮች ላይ ትጣ​ላ​ለህ።


ዓለም የማ​ይ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱ​ርና ተራራ ለተ​ራራ፥ ዋሻ ለዋ​ሻና ፍር​ኩታ ለፍ​ር​ኩ​ታም ዞሩ።


የም​ድ​ያ​ምም እጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከ​ረች፤ ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በተ​ራ​ሮ​ችና በገ​ደ​ሎች ላይ ጕድ​ጓ​ድና ዋሻ፥ ምሽ​ግም አበጁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ወደ እነ​ርሱ መሄድ እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋ​ሻና በግ​ንብ፥ በገ​ደ​ልና በቋ​ጥኝ፥ በጕ​ድ​ጓ​ድም ውስጥ ተሸ​ሸጉ።


ሁለ​ታ​ቸ​ውም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ገቡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም “እነሆ፥ ዕብ​ራ​ው​ያን ከተ​ሸ​ሸ​ጉ​በት ጕድ​ጓድ ይወ​ጣሉ” አሉ።


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር የተ​ሸ​ሸ​ጉት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እንደ ሸሹ በሰሙ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።


ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ።


跟着我们:

广告


广告