ኤርምያስ 40:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፤ በምድር ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ሲል ቃል ገባላቸው፤ “ለባቢሎናውያን መገዛት አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀምጣችሁ የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካም ይሆንላችኋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ለከለዳውያን ለማገልገል አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፥ መልካምም ይሆንላችኋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ገዳልያም እንዲህ ሲል ማለላቸው፦ “በእውነት ቃል ልግባላችሁ፤ ለባቢሎናውያን እጃችሁን ስለ መስጠት ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ በዚህች ምድር ሰፍራችሁ ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ለእናንተም ሁሉ ነገር መልካም ይሆንላችኋል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፥ በምድር ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፥ መልካምም ይሆንላችኋል። 参见章节 |