ኤርምያስ 40:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው አደረገ፤ እርሱን በድላችኋልና፥ ቃሉንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 አሁንም እግዚአብሔር አመጣው፤ እንደ ተናገረውም አደረገ። ይህ ሁሉ የሆነው እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና እርሱን ስላልታዘዛችሁ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጌታም አመጣው፥ እንደ ተናገረውም አደረገ፤ በጌታም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ድምፁንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር በእናንተ ላይ ሆነ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 አደርጋለሁ ብሎ ያቀደውን ሁሉ እነሆ አሁን ፈጽሞታል፤ ይህም ሁሉ የሆነው እናንተ ኃጢአት በመሥራታችሁና ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛችሁ ምክንያት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እግዚአብሔርም አመጣው እንደ ተናገረውም አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ቃሉንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ። 参见章节 |