Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 40:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ “እባ​ክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያ​ውቅ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን ልግ​ደ​ለው፤ ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ አይ​ሁድ ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ፥ የይ​ሁ​ዳም ቅሬታ እን​ዲ​ጠፋ ነፍ​ስ​ህን ስለ ምን ይገ​ድ​ላል?” ብሎ በመ​ሴፋ በቈ​ይታ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ተና​ገረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ “ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሄጄ ልግደለው፤ ሸሽተው ወደ አንተ የመጡት አይሁድ እንዲበተኑ፣ በይሁዳም የቀሩት እንዲጠፉ ለምን ይገድልሃል?” ብሎ በምጽጳ ለጎዶልያስ በምስጢር ነገረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ትሩፍ እንዲጠፋ አንተን ለምን ይገድላል?” ብሎ በምጽጳ በድብቅ ለጎዶልያስ ተናገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህም በኋላ ዮሐናን በምጽጳ በግል እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረገ ማን እንደ ሆነ ሳይታወቅ ሄጄ እስማኤልን ልግደለው፤ እንዴት እርሱ አንተን ሊገድልህ ይደፍራል? እርሱ ከገደለህ እኮ በዙሪያህ ለተሰበሰቡት አይሁድ መበታተን ምክንያት ይሆናል፤ በይሁዳ ምድር ከምርኮ በቀሩትም ሕዝብ ላይ ታላቅ ጥፋትን ያመጣል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ እባክህ፥ ልሂድ፥ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፥ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል? ብሎ በምጽጳ በቆይታ ለጎዶልያስ ተናገረ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 40:15
10 交叉引用  

እነ​ርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁ​ላ​ችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራ​ዊት ስለ​ሆ​ንህ ብን​ሸሽ ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና፥ እኩ​ሌ​ታ​ች​ንም ብን​ሞት ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና አት​ውጣ፤ አሁ​ንም መር​ዳ​ትን ትረ​ዳን ዘንድ በከ​ተማ ብት​ኖ​ር​ልን ይሻ​ለ​ናል” አሉት።


የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።


“ቤተ ሰቦቼ እኔ ስራ​ራ​ላ​ቸው፥ ሥጋ​ውን እን​በላ ዘንድ ማን በሰ​ጠን ብለው እንደ ሆነ፥


የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ር​ሔም ልጆች ዮሐ​ና​ንና ዮና​ታን፥ የተ​ን​ሁ​ሜ​ትም ልጅ ሠራያ፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የዮፌ ልጆች፥ የመ​ከጢ ልጅ አዛ​ን​ያም ከሰ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ወደ ጎዶ​ል​ያስ ወደ መሴፋ መጡ።


እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።


ምንም አት​መ​ክ​ሩም፤ ሕዝቡ ሁሉ ከሚ​ጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻ​ለ​ናል።”


በመ​ን​ገ​ድም አጠ​ገብ ወዳ​ሉት የበ​ጎች ማደ​ሪ​ያ​ዎች ወጣ፤ በዚ​ያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ወገ​ቡን ይሞ​ክር ዘንድ ወደ​ዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከዋ​ሻው በው​ስ​ጠ​ኛው ቦታ ተቀ​ም​ጠው ነበር።


አቢ​ሳም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ አሁ​ንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከም​ድር ጋር ላጣ​ብ​ቀው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ደ​ግ​መ​ውም” አለው።


跟着我们:

广告


广告