ኤርምያስ 40:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን በሰንሰለት አስሮ በወሰደው ጊዜ ከራማ ከለቀቀው በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን ኤርምያስን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ወደ ባቢሎን በሚወስዱት ምርኮኞች ሁሉ መካከል በራማ በሰንሰለት ታስሮ ባገኘው ጊዜ አስፈታው፤ ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን እርሱን በሰንሰለት አስሮ በመውሰድ ከራማ ከለቀቀው በኋላ፥ ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የክብር ዘብ አዛዡ ናቡዛርዳን እኔን በራማ ነጻ ከለቀቀኝ በኋላ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤ ከዚያ በፊት እኔ እዚያ የተወሰድኩት አሁን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ በመማረክ ታስረው ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ሕዝብ ሁሉ ጋር በሰንሰለት ታስሬ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በሰንሰለት አስሮ በወሰደው ጊዜ ከራማ ከለቀቀው በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። 参见章节 |