ኤርምያስ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ለአሕዛብ አሳስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላቶች ከሩቅ ሀገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤ ‘ከብበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ለአሕዛብ አሳውቁ፦ “እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በይሁዳ ከተሞች ላይ ጦርነትን እያወጁ ወራሪዎች ከሩቅ አገር በመምጣት ላይ መሆናቸውን ለሕዝቦች አሳውቁ! ለኢየሩሳሌም ሕዝብም ንገሩ! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ለአሕዛብ አሰሙና፦ እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ። 参见章节 |