Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 39:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የባቢሎን መንግሥት የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ወደ እርሱም ኮብልለው የነበሩትን ሰዎች፥ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማርኮ አፈለሳቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዛርዳን በከተማ የቀሩትን ሕዝብና ቀደም ብለው ወደ እርሱ ከድተው የገቡትንም ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በእስረኛነት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 39:9
20 交叉引用  

እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ሰዎች ግን ዮሴ​ፍን በግ​ብፅ ለፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ ለዘ​በ​ኞቹ አለቃ ለጲ​ጥ​ፋራ ሸጡት።


ከአ​ን​ተም ከሚ​ወ​ጡት ከም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆ​ችህ ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃን​ደ​ረ​ቦች ይሆ​ናሉ።”


የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።


የአ​በ​ዛ​ዎ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ማርኮ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት ወደ ዴብ​ላታ አመ​ጣ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቁ​ት​ምና፤ ብዙ​ዎቹ በረ​ኃ​ብና በውኃ ጥም ሞቱ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖ​ሩ​ትን በመ​ከራ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ሽም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፤ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በዚች ሀገር የሚ​ቀ​ሩ​ት​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅሬታ፥ በግ​ብ​ጽም ሀገር የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን በኰ​በ​ለሉ በአ​ይ​ሁድ እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ኛል፤ እነ​ር​ሱም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል ብዬ እፈ​ራ​ለሁ” አለው።


ወደ ባቢ​ሎን በተ​ማ​ረ​ኩት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች መካ​ከል የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን በሰ​ን​ሰ​ለት አስሮ በወ​ሰ​ደው ጊዜ ከራማ ከለ​ቀ​ቀው በኋላ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።


በየ​ሜ​ዳው የነ​በ​ሩት የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችና ሰዎ​ቻ​ቸው ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሀ​ገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ች​ንም፥ ወደ ባቢ​ሎን ያል​ተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም የም​ድ​ርን ድሆች እን​ዳ​ስ​ጠ​በቀ በሰሙ ጊዜ፥


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወስዶ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወዳ​ለ​በት ወደ ዴብ​ላታ ወሰ​ዳ​ቸው።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ መታ​ቸው፤ በኤ​ማ​ትም ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው፤ እን​ዲሁ ይሁዳ ከሀ​ገሩ ተማ​ረከ።


እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።


跟着我们:

广告


广告