Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 39:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በዚ​ያም ቀን አድ​ን​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው ሰዎች እጅ አል​ሰ​ጥ​ህም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አንተን ግን በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ለምትፈራቸው ሰዎች ዐልፈህ አትሰጥም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምትፈራቸውም ሰዎች እጅ ተላልፈህ አትሰጥም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ነገር ግን በዚያን ቀን እኔ እግዚአብሔር አንተን አድንሃለሁ፤ ለምትፈራቸው ጠላቶችህ ተላልፈህ አትሰጥም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 39:17
16 交叉引用  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


ዳዊ​ትም ጋድን፥ “በሁ​ሉም እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ በሰው እጅ ከም​ወ​ድቅ ይልቅ ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል” አለው።


ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።


አብ​ድ​ዩም ሄዶ አክ​ዓ​ብን ተገ​ና​ኘው፤ ነገ​ረ​ውም፤ አክ​ዓ​ብም ሮጦ ሄዶ ኤል​ያ​ስን ተገ​ና​ኘው።


እር​ሱም፥ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ካሉት ይበ​ል​ጣ​ሉና አት​ፍራ” አለው።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


ከአ​ንተ ጋር ይዋ​ጋሉ፤ ነገር ግን አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ድል አይ​ነ​ሡ​ህም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል የና​ታን ልጅ ሰፋ​ን​ያስ፥ የጳ​ስ​ኮ​ርም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ፥ የሰ​ሌ​ም​ያም ልጅ ዮካል፥ የመ​ል​ክ​ያም ልጅ ጳስ​ኮር ሰሙ።


“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ በመ​ጣ​ላ​ቸው በእ​ርሱ ላይ በአ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ እን​ጀራ ስለ​ሌለ በዚያ በራብ ይሞ​ታል።”


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


跟着我们:

广告


广告