Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 38:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ኤርምያስን ወስደው፣ በዘበኞች አደባባይ በነበረው በንጉሡ ልጅ በመልክያ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በገመድም ኤርምያስን ወደ ጕድጓዱ አወረዱት። ጕድጓዱም ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ዘልቆ ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኤርምያስንም ወሰዱት በግዞት ቤቱም አደባባይ ወደ ነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፥ ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፥ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 38:6
19 交叉引用  

ወስ​ደ​ውም ወደ ጕድ​ጓድ ጣሉት፤ ጕድ​ጓ​ዱም ውኃ የሌ​ለ​በት ባዶ ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ኝህ ነው፥ ነገ​ሥ​ታ​ትን በቍ​ጣው ቀን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥ ሕያ​ውም ያደ​ር​ገ​ዋል፥ በም​ድር ላይም ያስ​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፥ በጠ​ላ​ቶቹ እጅ አሳ​ልፎ አይ​ሰ​ጠ​ውም።


ነፍ​ሴን የሚ​ሹ​አት ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቍ​ሉም፥ ክፉ​ንም የሚ​መ​ክ​ሩ​ብኝ ወደ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።


በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር።


ንጉ​ሡም ጸሓ​ፊ​ውን ባሮ​ክ​ንና ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ይይዙ ዘንድ የን​ጉ​ሡን ልጅ ይረ​ሕ​ም​ኤ​ል​ንና የዓ​ዝ​ር​ኤ​ልን ልጅ ሠራ​ያን የዓ​ብ​ድ​ኤ​ል​ንም ልጅ ሰሌ​ም​ያን አዘዘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰወ​ራ​ቸው።


ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጕድ​ጓድ ቤት ወደ ጓዳ​ዎቹ ገባ፤ ኤር​ም​ያ​ስም በዚያ ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ አዘዘ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በግ​ዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖ​ሩት፤ እን​ጀ​ራም ሁሉ ከከ​ተማ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እን​ጀራ ከውጪ ጋጋ​ሪ​ዎች እያ​መጡ ይሰ​ጡት ነበር። እን​ዲ​ሁም ኤር​ም​ያስ በግ​ዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀ​ምጦ ነበር።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መዱ ጐተ​ቱት፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም አወ​ጡት፤ ኤር​ም​ያ​ስም በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


እነሆ በይ​ሁዳ ቤት የቀ​ሩ​ትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ያወ​ጣሉ፤ እነ​ዚ​ያም ሴቶች፦ ባለ​ሟ​ሎ​ችህ አታ​ል​ለ​ው​ሃል፤ አሸ​ን​ፈ​ው​ህ​ማል፤ እግ​ሮ​ችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነ​ርሱ ከአ​ንተ ወደ ኋላ ተመ​ል​ሰ​ዋል ይላሉ።


ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።


እር​ሱም ትእ​ዛ​ዙን ተቀ​ብሎ ወደ ውስ​ጠ​ኛው ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም በግ​ንድ አጣ​ብቆ ጠረ​ቃ​ቸው።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ አድ​ር​ጋ​ችሁ የተ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ተስፋ ታገኙ ዘንድ መታ​ገሥ ያስ​ፈ​ል​ጋ​ች​ኋል።


跟着我们:

广告


广告