Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 38:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን በኰ​በ​ለሉ በአ​ይ​ሁድ እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ኛል፤ እነ​ር​ሱም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል ብዬ እፈ​ራ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፣ “ወደ ባቢሎን የኰበለሉት አይሁድ እንዲያላግጡብኝ፣ ባቢሎናውያን ለእነርሱ አሳልፈው ይሰጡኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፦ “ወደ ከለዳውያን በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል እነርሱም ያፌዙብኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ንጉሡም “እኔ እኮ የምፈራው ከእኛ ከድተው ወደ ባቢሎን የገቡትን የአገራችንን ሰዎች ነው፤ ለእነርሱ አሳልፈው የሰጡኝ እንደ ሆነ ያሠቃዩኛል” ሲል መለሰልኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፦ ወደ ከለዳውያን በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል እነርሱም ያፌዙብኛል ብዬ እፈራለሁ አለው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 38:19
17 交叉引用  

መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ከከ​ተማ ወደ ከተማ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ ሀገር እስከ ዛብ​ሎን ሄዱ፤ እነ​ዚያ ግን በን​ቀት ሳቁ​ባ​ቸው፤ አፌ​ዙ​ባ​ቸ​ውም።


ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው።


ከብዙ ሕዝብ የተ​ነሣ በፊ​ታ​ቸው ለመ​ና​ገር አፍሬ እንደ ሆነ፥ ድሃ​ውም ከደጄ ባዶ​ውን ወጥቶ እንደ ሆነ፥


ሐሰት የተ​ና​ገ​ር​ሽው፥ እኔ​ንም ያላ​ሰ​ብ​ሽው፥ በል​ብ​ሽም ነገ​ሩን ያላ​ኖ​ር​ሽው ማንን ሰግ​ተሽ ነው? ማን​ንስ ፈር​ተሽ ነው? እኔም ዝም አል​ሁሽ፤ አን​ቺም አል​ፈ​ራ​ሽ​ኝም።


አቤቱ! አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ እኔም ተታ​ለ​ልሁ፤ ከእ​ኔም በረ​ታህ አሸ​ነ​ፍ​ህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳ​ቂያ ሆኛ​ለሁ፤ ሁሉም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል።


እነሆ በይ​ሁዳ ቤት የቀ​ሩ​ትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ያወ​ጣሉ፤ እነ​ዚ​ያም ሴቶች፦ ባለ​ሟ​ሎ​ችህ አታ​ል​ለ​ው​ሃል፤ አሸ​ን​ፈ​ው​ህ​ማል፤ እግ​ሮ​ችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነ​ርሱ ከአ​ንተ ወደ ኋላ ተመ​ል​ሰ​ዋል ይላሉ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ንጉሡ በእ​ና​ንተ ላይ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ል​ምና እነሆ በእ​ጃ​ችሁ ነው” አለ።


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።


ከሕ​ዝቡ አለ​ቆ​ችም ያመ​ኑ​በት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከም​ኵ​ራብ አስ​ወ​ጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ሰ​ዱ​አ​ቸው በፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ምክ​ን​ያት አል​መ​ሰ​ከ​ሩ​ለ​ትም።


ከዚ​ህም በኋላ ልባ​ቸ​ውን ደስ ባለው ጊዜ፥ “በፊ​ታ​ችን እን​ዲ​ጫ​ወት ሶም​ሶ​ንን ከእ​ስር ቤት ጥሩት” አሉ። ሶም​ሶ​ን​ንም ከእ​ስር ቤት ጠሩት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ተጫ​ወተ፤ ተዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትም፤ በም​ሰ​ሶና በም​ሰ​ሶም መካ​ከል አቆ​ሙት።


እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።


ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሕዝ​ቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላ​ቸ​ው​ንም ስለ ሰማሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና የአ​ን​ተን ቃል በመ​ተ​ላ​ለፍ በድ​ያ​ለሁ።


ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ወ​ጉ​ኝና እን​ዳ​ይ​ሳ​ለ​ቁ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።


跟着我们:

广告


广告