ኤርምያስ 38:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም” አለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ዐልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሏታል፤ አንተም ራስህ ከእጃቸው አታመልጥም።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ለእነርሱ እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ተላልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሉአታል፤ አንተም ማምለጥ አትችልም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም አለው። 参见章节 |