Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 37:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከእኔ ትጠ​ይቁ ዘንድ የላ​ካ​ች​ሁን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ እን​ዲህ በሉት፦ እነሆ ሊረ​ዳ​ችሁ የወ​ጣው የፈ​ር​ዖን ሠራ​ዊት ወደ ሀገሩ ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ትጠይቁኝ ዘንድ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ ‘ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሰራዊት ወደ ገዛ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔን እንድትጠይቁኝ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ ‘እነሆ፥ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ እነሆ፥ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 37:7
22 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ለላ​ካ​ችሁ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ግን እን​ዲህ በሉት፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ሰማ​ኸው ቃል፥


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ለግ​ብፅ ንጉሥ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበ​ርና የግ​ብፅ ንጉሥ ከዚያ ወዲህ ከሀ​ገሩ አል​ወ​ጣም።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


የግ​ብፅ ርዳታ ከን​ቱና ባዶ ነው፤ ስለ​ዚህ፥ “ምክ​ራ​ችሁ ከንቱ ነው” ብለህ ንገ​ራ​ቸው።


እነሆ፥ በዚያ በተ​ቀ​ጠ​ቀጠ በሸ​ን​በቆ በትር በግ​ብፅ ትታ​መ​ና​ለህ፤ ሰው ቢመ​ረ​ኰ​ዘው ተሰ​ብሮ በእጁ ይገ​ባል፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ሁሉ እን​ዲሁ ነው።


አሁ​ንስ የግ​ዮ​ንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግ​ብፅ መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወ​ን​ዞ​ች​ንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአ​ሦር መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ?


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ሽን አስ​ቈ​ር​ጦ​ሻ​ልና፥ በእ​ር​ሱም አይ​ከ​ና​ወ​ን​ል​ሽ​ምና እጅ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አድ​ር​ገሽ ከዚያ ደግሞ ትወ​ጫ​ለሽ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦


“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይወ​ጋን ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ምና​ል​ባ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአ​ም​ራቱ ሁሉ ያደ​ርግ እንደ ሆነ ስለ እኛ፥ እባ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቅ።”


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰ​ሌ​ም​ያን ልጅ ዮካ​ል​ንና ካህ​ኑን የማ​ሴ​ውን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ ላከ።


የፈ​ር​ዖ​ንም ሠራ​ዊት ከግ​ብፅ ወጣ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከብ​በ​ዋት የነ​በሩ ከለ​ዳ​ው​ያን ይህን ወሬ​አ​ቸ​ውን በሰሙ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።


ፌ። በማ​ያ​ድን ወገን እያ​መ​ንን ረዳ​ታ​ችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ጠፉ።


ብዙ​ዎ​ችን ነፍ​ሳት ለማ​ስ​ወ​ገድ ምሽ​ግን በመ​ሸጉ፥ ቅጥ​ር​ንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈር​ዖን በታ​ላቅ ኀይ​ልና በብዙ ሕዝብ በጦ​ር​ነት አይ​ረ​ዳ​ውም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እነ​ር​ሱን በተ​ከ​ተሉ ጊዜ እር​ስዋ በደ​ልን ታሳ​ስ​ባ​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ መታ​መኛ አት​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ ነኝ የጸ​ና​ች​ው​ንና የተ​ሰ​በ​ረ​ች​ው​ንም ክን​ዱን እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ሰይ​ፉ​ንም ከእጁ አስ​ጥ​ለ​ዋ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告