Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 37:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለመሆኑ፣ ‘የባቢሎን ንጉሥ እናንተንም ይህችንም ምድር አይወጋም’ ብለው ትንቢት ይናገሩ የነበሩት ነቢያታችሁ ወዴት ናቸው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ‘የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች አገር ላይ አይመጣም’ ብለው ትንቢት ለእናንተ ይናገሩ የነበሩ ነብዮቻችሁ ወዴት አሉ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ለመሆኑ ‘የባቢሎን ንጉሥ በአንተም ሆነ በአገርህ ላይ አደጋ አይጥልም’ ብለው የነገሩህ ነቢያትህ አሁን የት አሉ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች አገር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ?

参见章节 复制




ኤርምያስ 37:19
16 交叉引用  

ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባ​ትህ ነቢ​ያ​ትና ወደ እና​ትህ ነቢ​ያት ሂድ፥” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “አይ​ደ​ለም፤ በሞ​ዓብ እጅ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን ሦስት ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልን?” አለው።


ለአ​ንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸው አማ​ል​ክ​ትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸ​ውና ይነሡ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ያድ​ኑህ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በመ​ን​ገ​ዶ​ችዋ ቍጥር ለጣ​ዖት ሠዉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።


የሕ​ዝ​ቤ​ንም ስብ​ራት በጥ​ቂቱ ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


የሕ​ዝ​ቤ​ንም ሴት ልጅ ስብ​ራት በማ​ቃ​ለል ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤ ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤ ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት በሚ​ና​ገሩ በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ከገዛ ልባ​ቸ​ውም ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​ል​ካ​ቸው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይላል የሚሉ ሰዎች ሐሰ​ትን ያያሉ፤ ከን​ቱን ያም​ዋ​ር​ታሉ፤ ቃሉ​ንም ማጽ​ናት ይጀ​ም​ራሉ።


የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ስብ የም​ት​በ​ሉ​ላ​ቸው፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ች​ው​ንም ወይን የም​ት​ጠ​ጡ​ላ​ቸው፥ እነ​ርሱ ይነሡ፤ ይር​ዱ​አ​ች​ሁም፤ የሚ​ያ​ድ​ኑ​አ​ች​ሁም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


跟着我们:

广告


广告