Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 37:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አለ​ቆ​ችም በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተቈ​ጥ​ተው መቱት፤ የግ​ዞት ቤት አድ​ር​ገ​ውት ነበ​ርና ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዮና​ታን ቤት ላኩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መኳንንቱም እጅግ ተቈጥተው ኤርምያስን ደበደቡት፤ የግዞት ቤትም አድርገውት በነበረው፤ በጸሓፊው በዮናታን ቤት አሰሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አለቆችም ተቈጥተው ኤርምያስን መቱት፥ የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት የእስር ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ ቤት አስረው አኖሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እነርሱም በብርቱ ተቈጥተው ካስደበደቡኝ በኋላ የእስር ቤት እንዲሆን አድርገውት ወደነበረው ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት ውስጥ አስገብተው ዘጉብኝ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አለቆችም ተቈጥተው ኤርምያስን መቱት፥ የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት የግዞት ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ አኖሩት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 37:15
27 交叉引用  

ዮሴ​ፍ​ንም ወሰ​ደው፤ የን​ጉሡ እስ​ረ​ኞች ወደ​ሚ​ታ​ሰ​ሩ​በት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገ​ባው፤ ከዚ​ያም በግ​ዞት ነበረ።


አሳም በነ​ቢዩ በአ​ናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና በግ​ዞት አኖ​ረው፤ በዚ​ያን ጊዜም አሳ ከሕ​ዝቡ አያሌ ሰዎ​ችን አስ​ጨ​ነቀ።


እን​ዲ​ህም በሉ​አ​ቸው፦ ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት።”


አንተ ግን አቤቱ! ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ በላዬ የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር አት​በል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከፊ​ትህ አት​ደ​ም​ስስ፤ በፊ​ት​ህም ይው​ደቁ፤ በቍ​ጣህ ጊዜ እን​ዲሁ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።”


አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።


በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር።


አሁ​ንም አቤቱ ንጉሥ ሆይ! ልመ​ናዬ ወደ አንተ ይድ​ረስ፤ በዚያ እን​ዳ​ል​ሞት ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዮና​ታን ቤት አት​መ​ል​ሰኝ።”


እር​ሱ​ንም በግ​ዞት ቤት ገና አላ​ገ​ቡ​ትም ነበ​ርና ኤር​ም​ያስ በሕ​ዝቡ መካ​ከል ይወ​ጣና ይገባ ነበር።


አንተ በዚያ እሞት ዘንድ ወደ ዮና​ታን ቤት አት​መ​ል​ሰኝ ብዬ በን​ጉሡ ፊት ለመ​ንሁ” በላ​ቸው።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።


በግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባ​ይም ታስሮ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ሲል ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ፦


ገበሬዎቹም ባሮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ አንዱንም ገደሉት፤ ሌላውንም ወገሩት።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤


ሸፍ​ነ​ውም ፊቱን በጥፊ ይመ​ቱት ነበር፤ “ፊት​ህን በጥፊ የመ​ታህ ማነው? ንገ​ረን” እያ​ሉም ይጠ​ይ​ቁት ነበር።


ይህ​ንም ባለ​ጊዜ ከቆ​ሙት ሎሌ​ዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህ​ናቱ እን​ዲህ ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለ​ህን?” ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በጥፊ መታው።


እጃ​ቸ​ው​ንም በሐ​ዋ​ር​ያት ላይ አነሡ፤ ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ በሕ​ዝቡ ወኅኒ ቤትም አስ​ገ​ቧ​ቸው።


“በኢ​የ​ሱስ ስም ለማ​ንም እን​ዳ​ታ​ስ​ተ​ምሩ ከል​ክ​ለ​ና​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እነሆ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በት​ም​ህ​ር​ታ​ችሁ ሞላ​ች​ኋት፤ የዚ​ያ​ንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመ​ጡ​ብን ዘንድ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


እሺም አሰ​ኛ​ቸው፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ጠር​ተው ገረ​ፉ​አ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም በኢ​የ​ሱስ ስም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ገሥ​ጸው ተዉ​አ​ቸው።


ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告