Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 34:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገር ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ ስሜን አስ​ነ​ቀ​ፋ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው እን​ዲ​ሄዱ አር​ነት ያወ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ወን​ድና ሴት ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ኋ​ቸው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አረከሳችሁ፤ ወደ ፈለጉበት እንዲሄዱ ነጻ የለቀቃችኋቸውንም ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎቻችሁን መለሳችሁ፤ እንደ ገናም ባሪያዎቻችሁ አደረጋችኋቸው።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፥ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ አርነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችም እንዲሆኑላችሁ ገዛችኋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ነገር ግን እንደገና ሐሳባችሁን በመለወጥ ስሜን የሚያስነቅፍ ሥራ ሠራችሁ፤ ይኸውም ሁላችሁም እንደየፍላጎታቸው ነጻ የለቀቃችኋቸውን እንደገና ባሪያዎች አድርጋችሁ መግዛት ቀጠላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፥ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ አርነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባሪያዎቻችሁን አስመለሳችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም እንዲሆኑላችሁ ገዛችኋቸው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 34:16
15 交叉引用  

“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ነገር ግን ከዚያ በኋላ ተመ​ል​ሰው አር​ነት ያወ​ጡ​አ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን አስ​መ​ለሱ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም አድ​ር​ገው ገዙ​አ​ቸው።


እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤


ጻድቁ ግን ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ቢሠራ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ገው ርኵ​ሰት ሁሉ ቢያ​ደ​ርግ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልን? የሠ​ራው ጽድቅ ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ በአ​ደ​ረ​ገው ዐመ​ፅና በሠ​ራት ኀጢ​አት በዚ​ያች ይሞ​ታል።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱ​ሱን ስሜ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና በመ​ባ​ችሁ አታ​ር​ክሱ።


ደግሞ ጻድቁ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕን​ቅ​ፋት ባደ​ርግ፥ እርሱ ይሞ​ታል፤ አን​ተም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ው​ምና በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ያደ​ረ​ጋ​ትም የጽ​ድቅ ነገር አት​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ቅዱ​ሱም ስሜ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይታ​ወ​ቃል፤ ቅዱ​ሱ​ንም ስሜን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ረ​ክ​ስም፤ አሕ​ዛ​ብም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


በስ​ሜም በሐ​ሰት አት​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቅዱስ ስም አታ​ር​ክሱ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፣ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።


በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም፦ ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።


“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


跟着我们:

广告


广告