Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 33:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሌዋውያን ከሆኑት ካህናትም የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ፣ የእህል ቍርባን ለማቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ለመሠዋት ሁልጊዜ በፊቴ የሚቆም ሰው አይታጣም።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንዲሁም ሌዋውያን ካህናት በእኔ ፊት የሚቃጠለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ፥ የእህሉንም ቁርባን የሚያቃጥል፥ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ፈጽሞ አያጡም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንዲሁም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል መሥዋዕትና ሌላውንም መሥዋዕት በማቅረብ የሚያገለግሉኝ ካህናት ከሌዊ ወገን ከቶ አይጠፉም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 33:18
21 交叉引用  

ከዚ​ያም በኋላ ዘወ​ትር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የመ​ባ​ቻ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት፥ ሰውም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የሰ​ጠ​ውን ቍር​ባን አቀ​ረቡ።


ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል።


እና​ንተ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ትባ​ላ​ላ​ችሁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች ተብ​ላ​ችሁ ትጠ​ራ​ላ​ችሁ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ሀብት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሀ​ብ​ታ​ቸ​ውም ትመ​ካ​ላ​ችሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት መቍ​ጠር፥ የባ​ሕ​ር​ንም አሸዋ መስ​ፈር እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘርና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ኝን ሌዋ​ው​ያ​ንን አበ​ዛ​ለሁ።”


ስለ​ዚህ በፊቴ የሚ​ቆም ሰው ከሬ​ካብ ልጅ ከኢ​ዮ​ና​ዳብ ወገን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ጣም፥” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የጠ​በቁ የሳ​ዶቅ ልጆች ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀ​ር​ባሉ፤ ስቡ​ንና ደሙ​ንም ወደ እኔ ያቀ​ርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለሌ​ዋ​ው​ያን መኖ​ሪያ ርስት ከሃያ ዕቃ ቤቶች ጋር ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሲያ​ው​ቁት እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ነቱ አላ​ከ​በ​ሩ​ትም፤ አላ​መ​ሰ​ገ​ኑ​ት​ምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአ​ሳ​ባ​ቸ​ውም ረከሱ፤ ልቡ​ና​ቸ​ውም ባለ​ማ​ወቅ ጨለመ።


በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ።


“ለሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት፥ ለሌ​ዊም ነገድ ሁሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ድር​ሻና ርስት አይ​ኑ​ራ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት ድር​ሻ​ቸው ነው፤ እር​ሱን ይመ​ገ​ባሉ።


“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ተሸ​ክ​መ​ውት ባያ​ችሁ ጊዜ፥ ከሰ​ፈ​ራ​ችሁ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ተከ​ተ​ሉት።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告