Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 33:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “እነሆ ስለ እስ​ራ​ኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የሰ​ጠ​ሁ​ትን መል​ካም የተ​ስፋ ቃል የም​ፈ​ጽ​ም​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ተቃርቦአል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 33:14
31 交叉引用  

የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉም በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ ቃሌን ሰም​ተ​ሃ​ልና።”


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰባው ዓመት በባ​ቢ​ሎን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፥ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ችሁ ዘንድ መል​ካ​ሚ​ቱን ቃሌን እፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና በይ​ሁዳ ቤት የሰው ዘርና የእ​ን​ስሳ ዘር የም​ዘ​ራ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ዳ​መ​ጣሁ፥ እን​ዲሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ይህ​ችም ከተማ እኔ የም​ሠ​ራ​ላ​ቸ​ውን በጎ​ነት ሁሉ በሚ​ሰሙ፥ እኔም ስላ​መ​ጣ​ሁ​ላ​ቸው በጎ​ነ​ትና ሰላም ሁሉ በሚ​ፈ​ሩና በሚ​ደ​ነ​ግጡ አሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ለደ​ስታ፥ ለክ​ብ​ርና ለገ​ና​ን​ነት ትሆ​ና​ለች።”


“በዚያ ቀን የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት አነ​ሣ​ለሁ፤ የተ​ና​ደ​ው​ንም ቅጥ​ር​ዋን እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤ እንደ ቀደ​መ​ውም ዘመን እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ብዙ ነቢ​ያ​ትና ነገ​ሥ​ታት እና​ንተ የም​ታ​ዩ​ትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላ​ዩ​ምም፤ እና​ንተ የም​ት​ሰ​ሙ​ት​ንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አል​ሰ​ሙም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው ተስፋ ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አሜን እን​ላ​ለን።


ያለ እኛ ፍጹ​ማን እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን አስ​ቀ​ድሞ በይ​ኖ​አ​ልና።


ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።


跟着我们:

广告


广告