Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 29:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ስለ​ሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ስለ ቆልያ ልጅ፥ ስለ አክ​ዓ​ብና ሰለ ማሴው ልጅ ስለ ሴዴ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ፊት ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚነግሯችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፤ “እነዚህን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም ዐይናችሁ እያየ ይገድላቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ‘በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚነግሩአችሁ፥ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ በዐይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “በእግዚአብሔር ስም የሐሰት ትንቢት ቃል ስለሚነግሩአችሁም ስለ ቆላያ ልጅ አክዓብና ስለ ማዕሤያ ልጅ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ ‘እነርሱን ዐይናችሁ እያየ በፊታችሁ በሞት ለሚቀጣቸው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ በዓይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 29:21
8 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ አን​ተን ከወ​ዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ጋር አፈ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሰይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ያያሉ፤ አን​ተ​ንና ይሁ​ዳ​ንም ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ወደ ባቢ​ሎን ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።


አን​ተም ጳስ​ኮር ሆይ! በቤ​ት​ህም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ተማ​ር​ካ​ችሁ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ፤ አን​ተም በሐ​ሰት ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያም ትቀ​በ​ራ​ላ​ችሁ።”


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።


“እና​ን​ተም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ቢ​ሎን ነቢ​ያ​ትን አስ​ነ​ሥ​ቶ​ል​ናል ብላ​ች​ኋ​ልና፤


ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤ ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤ ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል።


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤


跟着我们:

广告


广告