Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 29:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይ​ፍ​ንና ራብን፥ ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከመ​ጐ​ም​ዘ​ዙም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉ በለስ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በርግጥ እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍን፣ ራብንና መቅሠፍትን እሰድድባቸዋለሁ፤ ከመበላሸቱ የተነሣም ሊበላ እንደማይቻል እንደ መጥፎ የበለስ ፍሬ አደርጋቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም በመካከላቸው እልክባቸዋለሁ፥ ከክፋቱም የተነሣ ሊበላ እንደማይችል እንደ ተበላሸ በለስ አደርጋቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በእነርሱ ላይ ጦርነትን፥ ራብንና ቸነፈርን ላመጣባቸው ነው፤ ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበሉት እንደማይቻል የበለስ ዛፍ ፍሬ አደርጋቸዋለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም እሰድድባቸዋለሁ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 29:17
14 交叉引用  

“ለባ​ቢ​ሎን ንጉ​ሥም ለና​ቡ​ከ​ን​ደ​ነ​ፆር የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሕዝ​ብና መን​ግ​ሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ ለር​ግ​ማ​ንና ለጥ​ፋት፥ ለማ​ፍ​ዋ​ጫም፥ ለመ​ሰ​ደ​ቢ​ያም እን​ዲ​ሆኑ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ዘንድ ለመ​በ​ተን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።


መጥ​ቶም የግ​ብ​ፅን ምድር ይመ​ታል፤ ለሞ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሞት፥ ለም​ር​ኮም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለም​ርኮ፥ ለሰ​ይ​ፍም የሚ​ሆ​ነ​ውን ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ወር በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀ​ገ​ሩም ሰዎች እን​ጀራ ታጣ።


በየ​ሀ​ገሩ ታላቅ የም​ድር መነ​ዋ​ወ​ጥና ራብ፥ በሰ​ውም ላይ በሽ​ታና ፍር​ሀት ይመ​ጣል፤ በሰ​ማ​ይም ታላቅ ምል​ክት ይሆ​ናል።


ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀ​ነ​ሱና ለሚ​ያ​ጠቡ ወዮ​ላ​ቸው፤ በም​ድር ላይ ጽኑ መከራ፥ በዚ​ህም ሕዝብ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ና​ልና።


አየሁም፤ እነሆም ሐመር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።


跟着我们:

广告


广告