ኤርምያስ 27:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤ እስከምጐበኛቸው ቀን ድረስ በዚያ ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በዚያን ጊዜም ትወጣላችሁ፤ ወደዚህም ስፍራ ትመለሳላችሁ።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ‘ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቀመጣሉ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በዚያ ጊዜም እመልሳቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ አመጣቸዋለሁ።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፥ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቆያሉ፥ ይላል ጌታ፤ ከዚያም በኋላ አውጥቼአቸው ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሐሳቤን ወደ እነርሱ እስከምመልስበት ጊዜ ድረስ፥ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ወደ ባቢሎን ተወስደው በዚያ ይኖራሉ። ከዚያም በኋላ እንደገና መልሼ ወደዚህ ስፍራ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ወደ ባቢሎን ትወሰዳለች እስከምጐበኛትም ቀን ድረስ በዚያ ትኖራለች፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያን ጊዜም አወጣታለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳታለሁ። 参见章节 |