ኤርምያስ 25:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም፤ አይቀበሩምም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 በዚያ ጊዜ በእግዚአብሔር የተገደሉት ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር በሁሉ ስፍራ ተረፍርፈው ይታያሉ፤ እንደ ጕድፍ በምድር ላይ ይጣላሉ እንጂ፣ አይለቀስላቸውም፤ ሬሳቸውም አይሰበሰብም፤ አይቀበርምም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 በዚያም ቀን ጌታ የገደላቸው ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 በዚያን ቀን እግዚአብሔር በሞት የሚቀጣቸው ሰዎች ሬሳ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ይረፈረፋል፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ ሰብስቦ የሚቀብራቸው አያገኙም፤ ስለዚህ እንደ ጥራጊ በሜዳ ላይ ተጥለው ይቀራሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፥ አይለቀስላቸውም፥ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይከማቹም አይቀበሩምም። 参见章节 |