Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ክር​ክር አለ​ውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋ​ረ​ዳል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋራ ይፋረዳልና፣ ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ያስተጋባል፤ በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያመጣል፤ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጌታ ከአሕዛብ ጋር ሙግት አለውና ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚገሥጽበት ጊዜ የሚያሰማው ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል፤ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይፈርዳል፤ ክፉዎችንም በሞት ይቀጣል፤’ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፥ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:31
14 交叉引用  

ከቃ​ልህ ግርማ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ፈር​ተው ሸሹ፤ አሕ​ዛ​ብም ተበ​ተኑ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ነውና፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ያጠ​ፋ​ቸ​ውና ለጦር ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ በቍ​ጥ​ራ​ቸው ልክ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ርዱ ቀን፥ ስለ ጽዮ​ንም ፍርድ የብ​ድ​ራት ዓመት ነውና።


ምድ​ርም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰ​ይፉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተቀ​ሥ​ፈው የሞ​ቱት ይበ​ዛሉ።


አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእ​ው​ነት ቍጣው ከእኔ ይመ​ለስ አልሽ። እነሆ ኀጢ​አት አል​ሠ​ራ​ሁም ብለ​ሻ​ልና እፋ​ረ​ድ​ሻ​ለሁ።


እነሆ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ንው​ጽ​ው​ጽታ ይመ​ጣል፤ ኃጥ​ኣ​ንን ያነ​ዋ​ው​ጣ​ቸ​ውና ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸው ዘንድ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋል፤ የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ራስ ይገ​ለ​ባ​ብ​ጣል።


ለራ​ስህ ታላ​ላቅ ነገ​ሮ​ችን ትፈ​ል​ጋ​ለ​ህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለ​ሁና አት​ፈ​ል​ጋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በሄ​ድ​ህ​በት ስፍራ ሁሉ ነፍ​ስ​ህን እንደ ምርኮ አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደ​መና ቀን፥ የአ​ሕ​ዛብ ማለ​ቂያ ጊዜ ይሆ​ናል።


በቸ​ነ​ፈ​ርና በደም እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ዶፍም፥ የበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ፥ እሳ​ትና ድኝም በእ​ር​ሱና በጭ​ፍ​ሮቹ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


ኤፍ​ሬም ግን ክብ​ር​ንና ከንቱ ነገ​ርን የሚ​ያ​ሳ​ድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁል​ጊ​ዜም ሐሰ​ት​ንና ተን​ኰ​ልን ያበ​ዛል፤ ከአ​ሦ​ርም ጋር ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋል፤ ምሕ​ረ​ትም ያደ​ር​ጉ​ለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይ​ትን ይል​ካል።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።


跟着我们:

广告


广告