Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በእ​ር​ስ​ዋም ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ቃሌን ሁሉ፥ ኤር​ም​ያስ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ በት​ን​ቢት የተ​ና​ገ​ረ​ውን በዚች መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ፥ በዚ​ያች ምድር ላይ አመ​ጣ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በምድሪቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ ይኸውም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውንና ኤርምያስ በሕዝቦች ሁሉ ላይ የተናገረውን ትንቢት አመጣባታለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በእርሷም ላይ የተናገርሁትን ቃሎቼን ሁሉ፥ ማለት ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ትንቢት የተናገረውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ፥ በዚያች ምድር አመጣለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በኤርምያስ አማካይነት በሕዝብ ሁሉ ላይ አመጣለሁ ያልኩትን፥ ማለትም በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ሁሉ በላይዋ ላይ በማውረድ ባቢሎንን እቀጣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በእርስዋም ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፥ ማለት ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ትንቢት የተናገረውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ፥ በዚያች ምድር አመጣለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:13
10 交叉引用  

ከአፌ የሚ​ወጣ ቃሌ እን​ዲሁ ነው፤ የም​ሻ​ውን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ወደ እኔ በከ​ንቱ አይ​መ​ለ​ስም፤ መን​ገ​ዴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን አከ​ና​ው​ና​ለሁ።


እነሆ ትነ​ቅ​ልና ታፈ​ርስ ዘንድ፥ ታጠ​ፋና ትገ​ለ​ብጥ ዘንድ፥ ትሠ​ራና ትተ​ክል ዘንድ በአ​ሕ​ዛ​ብና በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ላይ ዛሬ ሾሜ​ሃ​ለሁ።”


“በእ​ና​ትህ ሆድ ሳል​ሠ​ራህ አው​ቄ​ሃ​ለሁ፤ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ሳት​ወጣ ቀድ​ሼ​ሃ​ለሁ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነቢይ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።”


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፍ።


“አንድ የመ​ጽ​ሐፍ ክር​ታስ ውሰድ፥ ለአ​ን​ተም ከተ​ና​ገ​ር​ሁ​በት ቀን ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ጻፍ​በት።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄ​ምን እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በር​ግጥ ይመ​ጣል፤ ይች​ንም ሀገር ያፈ​ር​ሳ​ታል፤ ሰውና እን​ስ​ሳም ያል​ቃሉ ብለህ ለምን ጻፍ​ህ​በት? ብለህ ይህን ክር​ታስ አቃ​ጥ​ለ​ሃል።


ኤር​ም​ያ​ስም የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክን ጠራ፤ ባሮ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ርሱ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ በመ​ጽ​ሐፉ ክር​ታስ ጻፈ።


“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል፤” ተባልሁ።


跟着我们:

广告


广告