Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ደ​ዚህ እንደ መል​ካሙ በለስ፥ እን​ዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሰ​ደ​ድ​ሁ​ትን የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ለበ​ጎ​ነት እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፣ ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎናውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳ ምርኮ በመልካም አስበዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የላክሁትን የይሁዳን ምርኮ በበጐነት እመለከተዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ወደ ባቢሎን የላክኋቸውን ሕዝብ እንደነዚህ ጥሩ የበለስ ፍሬዎች እንደ ሆኑ እቈጥራለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለበጐነት እመለከተዋለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 24:5
21 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ለእ​ና​ንተ የማ​ስ​ባ​ትን አሳብ እኔ አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፍጻ​ሜና ተስፋ እሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሰ​ላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይ​ደ​ለም።


ስለ​ዚህ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን የሰ​ደ​ድ​ኋ​ችሁ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ላስ​ማ​ረ​ክ​ኋ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ሁሉ እን​ዲህ ይላል፦


ስለ​ዚ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምድር እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በት​እ​ዛ​ዜም ይሄዱ ዘንድ፥ ፍር​ዴ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ እነ​ርሱ ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፥ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ነኝና እነ​ርሱ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ሳሉ፥ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያለ​ኝን ቃል ኪዳን እስ​ካ​ፈ​ርስ ድረስ አል​ጥ​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ጸ​የ​ፋ​ቸ​ው​ምም።


እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


እርሱ ግን መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም፤’ አለ።


የእኔ የሆኑ በጎች ግን ቃሌን ይሰ​ሙ​ኛል፤ እኔም አው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይከ​ተ​ሉ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ወድ ሰው ግን እርሱ በእ​ርሱ ዘንድ በእ​ው​ነት የታ​ወቀ ነው።


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐወ​ቃ​ች​ሁት፤ ይል​ቁ​ንም እርሱ ዐወ​ቃ​ችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደ​ዚያ ወደ ደካ​ማው፥ ወደ ድሀው ወደ​ዚህ ዓለም ጣዖት ተመ​ል​ሳ​ችሁ፥ ትገ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ዴት ፈጠ​ራን ትሻ​ላ​ችሁ?


በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን መል​ካም ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ ሊፈ​ት​ንህ፥ ሊያ​ዋ​ር​ድ​ህም አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቁ​ትን መና በም​ድረ በዳ የመ​ገ​በ​ህን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ፥


ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


跟着我们:

广告


广告