Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 23:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ስለ​ዚህ እነሆ እያ​ን​ዳ​ንዱ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቃሌን በሚ​ሰ​ርቁ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “ስለዚህ ቃሌን እርስ በእርስ በመሰራረቅ ከእኔ እንደ ተቀበሉ አድርገው የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ስለዚህ፥ እነሆ፥ አንዱ ከሌላው ዘንድ ቃሎቼን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አንዱ ከሌላው ቃልን በመስረቅ ‘ይህ የእግዚአብሔር ቃል ነው’ እያሉ የሚናገሩትን ነቢያት እጠላለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ስለዚህ፥ እነሆ፥ እያንዳንዱ ከባልንጀራው ዘንድ ቃሌን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 23:30
14 交叉引用  

ፈተ​ኑኝ፥ በእኔ ላይም ዘበ​ቱ​ብኝ፥ ሣቁ​ብ​ኝም፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አን​ቀ​ጫ​ቀጩ።


እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድን​ጋ​ያማ ሸለቆ የም​ት​ቀ​መጥ ሆይ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እና​ን​ተም፦ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠን ወይም ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችን የሚ​ገባ ማን ነው? የም​ትሉ ሆይ! እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፤


እነሆ ከም​ላ​ሳ​ቸው ትን​ቢ​ትን አው​ጥ​ተው፦ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢ​ያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


“ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁ​ዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክ​ፋት በላ​ያ​ችሁ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“ቃሌም በላ​ያ​ችሁ ለክ​ፋት እን​ዲ​ጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እን​ደ​ም​ጐ​በ​ኛ​ችሁ ምል​ክ​ታ​ችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍ​ሳ​ትን እንደ ወፍ በም​ታ​ጠ​ም​ዱ​ባት በመ​ከ​ዳ​ችሁ ላይ ነኝ፤ ከክ​ን​ዳ​ች​ሁም ወስጄ እቀ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ እንደ ወፍም የም​ታ​ጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት እለ​ቅ​ቃ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገ​ርን ስለ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ሐሰ​ተኛ ራእ​ይ​ንም ስለ አያ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ፊቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ ከእ​ሳ​ትም አይ​ወ​ጡም፤ እሳ​ትም ይበ​ላ​ቸ​ዋል፤ ፊቴ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ በአ​ጸ​ናሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


መቅ​ደ​ሴን ያረ​ክስ ዘንድ፥ የቅ​ዱ​ሳ​ኔ​ንም ስም ያጐ​ስ​ቍል ዘንድ ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ሰጥ​ቶ​አ​ልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


ነገር ግን ይና​ገር ዘንድ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል በስሜ የሚ​ና​ገር ነቢይ፥ በሌላ አማ​ል​ክት ስም የሚ​ና​ገር ነቢ​ይም፥ እርሱ ይገ​ደል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ፥ ቅን​አ​ቱም በዚያ ሰው ላይ ይነ​ድ​ዳል እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም፤ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈው ርግ​ማን ሁሉ በላዩ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስ​ሰ​ዋል።


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”


跟着我们:

广告


广告