ኤርምያስ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና የካህኑን የመዕሴይን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እንዲህም አለ፦ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ የመልክያን ልጅ ፋስኮርን እንዲሁም የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እርሱ በላከ ጊዜ፣ ቃል ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጣ፤ የተላኩትም እንዲህ ብለውት ነበር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል በላከበት ጊዜ ነው፦ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ፓሽሑርንና የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እኔ ልኮ እንዲህ ሲል አስጠየቀኝ፦ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። 参见章节 |