Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አን​ቺስ፦ አል​ረ​ከ​ስ​ሁም፤ በዓ​ሊ​ም​ንም አል​ተ​ከ​ተ​ል​ሁም፤ እን​ዴት ትያ​ለሽ? በሸ​ለቆ ያለ​ውን መን​ገ​ድ​ሽን ተመ​ል​ከቺ፤ ያደ​ረ​ግ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመ​ን​ገ​ዶች ትጮ​ኻ​ለች፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ ‘አልረከስሁም፣ በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ እስኪ አስቢ፣ ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤ እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ታዲያ ‘ራሴን ከቶ አላረክስም፤ ለበዓልም ከቶ አልሰግድም’ ብለሽ ለማስተባበል እንዴት ትችያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ኃጢአት በመሥራት ያደረግሽውን ርኲሰት እስቲ ተመልከቺ፤ በፍትወት እንደ ተቃጠለች የበረሓ ግመል፥ ወዲያና ወዲህ ትባዝኚአለሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አንቺስ፦ አልረከስሁም በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ? በቈላ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ያደረግሽውንም እወቂ፥ በመንገድም ላይ እንደ ተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ሆነሻል፥

参见章节 复制




ኤርምያስ 2:23
24 交叉引用  

እንደ ሣር ፈጥ​ነው ይደ​ር​ቃ​ሉና፥ እንደ ለመ​ለመ ቅጠ​ልም ፈጥ​ነው ይረ​ግ​ፋ​ሉና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዚህ ሕዝብ እን​ዲህ ይላል፥ “መቅ​በ​ዝ​በ​ዝን ወድ​ደ​ዋል፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም አል​ከ​ለ​ከ​ሉም፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ርሱ ደስ አይ​ለ​ውም፤ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አሁን ያስ​ባል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይጐ​በ​ኛል።”


“ለዚ​ህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገ​ርን ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረ​ብን? በደ​ላ​ች​ንስ ምን​ድን ነው? በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? ቢሉህ፥


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን አቅ​ን​ተሽ አንሺ፤ ያል​ተ​ጋ​ደ​ም​ሽ​በት ስፍራ እን​ዳ​ለም ተመ​ል​ከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራ​ዎች በመ​ን​ገድ ላይ ተቀ​ም​ጠሽ በዝ​ሙ​ት​ሽና በክ​ፋ​ትሽ ምድ​ሪ​ቱን አር​ክ​ሰ​ሻ​ታ​ልና።


አንቺ ከዳ​ተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዣ​ለሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥ​ሮ​አ​ልና ሰው ወደ ድኅ​ነት ይመ​ጣል።”


እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ያለ​ች​ውን የቶ​ፌ​ትን መሥ​ዊ​ያ​ዎች ሠር​ተ​ዋል።


ነገር ግን የል​ባ​ቸ​ውን ምኞ​ትና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ያስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖት ተከ​ት​ለ​ዋል፤


ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃሉ መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆሴ​ዕን፥ “ምድ​ሪቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቃ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለ​ችና ሂድ፤ ዘማ​ዊ​ቱን ሴትና የዘ​ማ​ዊ​ቱን ልጆች ለአ​ንተ ውሰድ” አለው።


ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


跟着我们:

广告


广告